Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 1:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ይህን ሁሉ አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙ​ሴና ለአ​ሮን ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 1:54
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እንግዲህ እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ አድርግ፤ በእርሱ ላይ ምንም ነገር አትጨምር፤ ከእርሱም አንዳች ነገር አታጒድል።


ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ አስተምሩአቸው! እነሆ፥ እኔም እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የሚወደው የቱን ይመስልሃል? መታዘዝን ወይስ ቊርባንና መሥዋዕት ማቅረብን? ለእርሱ መታዘዝ ምርጥ የበግ መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤


በዚህ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ፤ እያንዳንዱ ነገድ ዓርማውን በመከተል ይሰፍር ነበር፤ እያንዳንዱም በየቤተሰቡ ተመድቦ ይጓዝ ነበር።


ወደ ድንኳኑ በሚገቡበትና ወደ መሠዊያው በሚቀርቡበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ይህን ማድረግ ነበረባቸው።


ሙሴም ልክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረገ።


ሙሴም ሁሉን ነገር መርምሮ ልክ እግዚአብሔር ባለው መሠረት መሥራታቸውን አረጋገጠ፤ ስለዚህም ሙሴ ባረካቸው።


በመጨረሻም የመገናኛው ድንኳን አሠራር በሙሉ ተፈጸመ፤ እስራኤላውያን ሁሉን ነገር እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ፤


ነገር ግን ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ በመቅረብ ቊጣዬን አነሣሥቶ የእስራኤልን ማኅበር እንዳያስፈጅ ሌዋውያን በድንኳኑ ዙሪያ ሰፍረው ይጠብቁት።”


እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦


ሄደውም በሙሴና በአሮን አማካይነት እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ።


በዚህም ዐይነት ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በሲና በረሓ ሕዝቡን ቈጠረ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፥ ሙሴና አሮን እንዲሁም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሌዋውያንን ቀደሱ።


እነርሱም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን በምሽት በሲና ምድረ በዳ በዓሉን አከበሩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።


ሁለት ቀንም ይሁን አንድ ወር፥ አንድ ዓመትም ይሁን ከዚያ የረዘመ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ አይንቀሳቀሱም ነበር፤ ደመናው ሲነሣ ግን ጒዞአቸውን ይቀጥሉ ነበር።


የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች