Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 8:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እርሱም “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ስለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ኢየሱስም፣ “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፤ ለምን ይህን ያህል ፈራችሁ?” አላቸው፤ ከዚያም ተነሥቶ ነፋሱንና ማዕበሉን ገሠጸ፤ ወዲያውም ጸጥታ ሰፈነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸው፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እርሱም፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 8:26
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከባሕሩ መናወጥ የተነሣ የሚያስገመግመውን የማዕበል ድምፅ ጸጥ ታደርጋለህ፤ የሕዝቦችንም ሁከት ዝም ታሰኛለህ።


አንተ የባሕሩን መናወጥ በሥልጣንህ ታዛለህ፤ ማዕበሉንም ጸጥ ታደርጋለህ።


ታዲያ ዛሬ ታይቶ ነገ በእሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር፥ እግዚአብሔር እንዲህ የሚያለብስ ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም!


በእምነቱ ብርቱ ሆኖ ለእግዚአብሔር ክብር ሰጠ እንጂ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ባለማመን ከቶ አልተጠራጠረም።


ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ‘እንጀራ ስላልያዝን ነው’ ብላችሁ ስለምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ?


የተከፈተች ትንሽ የብራና ጥቅል መጽሐፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፥ ግራ እግሩንም በምድር ላይ አኖረ፤


እግዚአብሔር ሆይ! ፈረሶችህንና ሠረገላዎችህን ወደ ድል በመራኸቸው ጊዜ፥ ኀይለኛው ቊጣህ በወንዞች ላይ ነበርን? ወይስ በባሕሩ ላይ ተቈጥተህ ነበርን?


እግዚአብሔር ባሕሩንና ወንዞቹን ገሥጾ ያደርቃቸዋል። በባሳንና በቀርሜሎስ የሚገኙ ዕፀዋት ይደርቃሉ፤ የሊባኖስም አበቦች ይጠወልጋሉ።


ለራሱ ዘለዓለማዊ ስም ይሆን ዘንድ በፊታቸው ውሃን ለመክፈል ክብርን የተመላ ኀይሉን በሙሴ ቀኝ በኩል እንዲራመድ ያደረገው የት አለ?


ሰዎቹም ተደንቀው፥ “ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” አሉ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እምነታችሁ ጐደሎ ስለ ሆነ ነው፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወዲያ ሂድ!’ ብትሉት ይሄዳል፤ የሚሳናችሁም ምንም ነገር አይኖርም።


ኢየሱስም ርኩሱን መንፈስ፥ “ዝም ብለህ ከእርሱ ውጣ!” ሲል ገሠጸው፤ ርኩሱ መንፈስ ሰውየውን በሕዝቡ ፊት ጣለውና ምንም ሳይጐዳው ወጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች