Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 6:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በዚህ አኳኋን፥ መጾምህን በስውር ካለው አባትህ በቀር ሌላ ማንም አያውቅም። በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በዚህም መጾምህ በስውር ያለው አባትህ ብቻ የሚያውቀው፣ ከሰዎች ግን የተሰወረ ይሆናል፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በስውር ላለው አባትህ እንጂ በሰዎች ዘንድ ጾመኛ ሆነህ እንዳትታይ፤ በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 6:18
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንግዲህ ምጽዋትህ በስውር ይሁን፤ በስውር የተሠራውን የሚያየው አባትህ፥ የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።


አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ ክፍልህ ገብተህ፥ በርህን ዝጋና በስውር ወዳለው ወደማይታይ አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።


እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደየሥራው ይሰጠዋል።


ሰው ለመመስገን የሚበቃው ጌታ ሲያመሰግነው ነው እንጂ ራሱን በራሱ ሲያመሰግን አይደለም።


ከዚህ ከሥጋችን ጋር ብንሆንም ወይም ከእርሱ ብንለይም ዓላማችን ጌታን ማስደሰት ነው።


ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።


ስለ ጌታ ኢየሱስ ብላችሁ ሥልጣን ለተሰጣቸው ሕዝባዊ ድርጅቶች ታዘዙ፤ የበላይ ባለሥልጣን ስለ ሆነ ለንጉሠ ነገሥቱም ታዘዙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች