Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ስለ ሆነች በመንፈሳዊ ኑሮአቸው ድኾች መሆናቸው የሚሰማቸው የተባረኩ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “ንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 5:3
55 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነዚህን ሁሉ ነገሮች የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ ስለዚህ ሁሉም የእኔ ናቸው፤ እኔ የምመለከተው ልባቸው ወደ ተሰበረ፥ ትሑት መንፈስ ወዳላቸውና፥ ቃሌንም ወደሚያከብሩ ነው።


ትምክሕተኛነት ወደ ውድቀት ያደርስሃል፤ ትሑት ከሆንክ ግን ትከበራለህ።


ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል።


ከትዕቢተኞች ጋር የዘረፉትን አብሮ ከመካፈል ትሑት ሆኖ በድኽነት መኖር ይሻላል።


ጽድቅን አግኝቶ ወደ ቤቱ የተመለሰው ይህ ቀራጭ ነው እንጂ ፈሪሳዊው አይደለም እላችኋለሁ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ግን ከፍ ይላል።”


በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ እስራኤላውያን ራሳቸውን አዋርደው ከሚያደርጉት ክፉ ነገር በመራቅ ተጸጽተውና ንስሓ ገብተው ወደ እኔ ቢጸልዩ በሰማይ ሆኜ እሰማቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤ ምድራቸውም እንደገና ፍሬያማ እንድትሆን አደርጋለሁ፤


ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት የተሰበረ ልብ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።


ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


ለተጨቈኑት መልካም ዜናን አበሥር ዘንድ፥ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩት ነጻነትን፥ ለታሰሩት መፈታትን ለማወጅ እግዚአብሔር ቀብቶ ስለ ላከኝ፥ የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው።


እኔ ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን እንዴት እንደምቀጣ በሰማህ ጊዜ፥ ራስህን አዋርደኽ በሐዘን ልብስህን በመቅደድና በማልቀስ ንስሓ ገብተሃል፤ ስለዚህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።


እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።


ኢየሱስ ግን “የተባረኩስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው በሥራ ላይ የሚያውሉት ናቸው፤” አላት።


እግዚአብሔር ይመስገን! እግዚአብሔርን የሚፈራና ትእዛዞቹንም በመፈጸም እጅግ ደስ የሚለው ሰው እንዴት የተባረከ ነው!


በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ የኃጢአተኞችን መንገድ የማይከተል፥ ከፌዘኞች ጋር ኅብረት የማያደርግ የተባረከ ነው።


ከዚህም የተነሣ የተናገርኩት ነገር ስላሳፈረኝ በዐመድና በትቢያ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህን ነገር ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለአላዋቂዎች ስለ ገለጥክላቸው አመሰግንሃለሁ፤


“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቈኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤


ኢየሱስም ይህን በማየት ተቈጥቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ ተዉ፤ አትከልክሉአቸው፤


“የእናንተ ግን ዐይኖቻችሁ ስለሚያዩ፥ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ የተባረኩ ናቸው።


ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።”


የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነለትና በአምላኩ በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረገ ሰው ደስ ይበለው፤


ምናሴ ሥቃይ በበዛበት ጊዜ ራሱን በትሕትና በማዋረድ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርንም ርዳታ ለመነ፤


ድኾችን የሚረዱ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል።


ቊጣው በቅጽበት ስለሚነድ በእናንተ ላይ ተቈጥቶ እንዳያጠፋችሁ በመንቀጥቀጥ ስገዱለት እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።


አባቱ እንዳደረገው ሁሉ ራሱን በትሕትና ዝቅ አድርጎ በማዋረድ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤ እንዲያውም ከአባቱ ይበልጥ የከፋ ኃጢአት ሠራ።


ጌታ በቃል ኪዳኑ መሠረት ለወዳጆቹ የሚሰጠውን የሕይወት አክሊል ስለሚቀበል ፈተናን ታግሦ የሚጸና ሰው የተባረከ ነው።


ኢየሱስም ቶማስን፥ “አንተስ ስለ አየኸኝ አመንክ፤ ሳያዩኝ የሚያምኑ ግን የተመሰገኑ ናቸው” አለው።


ጌታው በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ አገልጋይ የተባረከ ነው።


የሠራዊት አምላክ ሆይ! በአንተ የሚታመኑ እንዴት የተባረኩ ናቸው!


አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።


የሰው ሀብት እንደ ሣር አበባ ስለሚረግፍ በኑሮው ከፍ ያለ ወንድም እግዚአብሔር በኑሮው ዝቅ ቢያደርገውም ደስ ይበለው፤


“ልጆቼ ሆይ! አድምጡኝ መንገዴን የሚከተሉ ይደሰታሉ።


ንጉሥ ምናሴ ወደ እግዚአብሔር ያቀረበው ጸሎትና፥ እግዚአብሔርም ለጸሎቱ የሰጠው መልስ፥ ተጸጽቶ ንስሓ ከመግባቱ በፊት ያደረገው ኃጢአት ሁሉ፥ ማለትም የፈጸመው ልዩ ልዩ ክፋት፥ እርሱ ራሱ የሠራቸው የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና አሼራ ተብላ የምትጠራው ሴት አምላክ ምስሎች፥ ያመልካቸው የነበሩ ጣዖቶች ሁሉ፥ በነቢያት የታሪክ መጻሕፍት ውስጥ ተመዝግበው ይገኛሉ።


ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ለመብላትና በደጃፎችዋም ወደ ከተማይቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን ያጠቡ የተባረኩ ናቸው።


ከዚህ በኋላ መልአኩ “ወደ በጉ ሠርግ ግብዣ የተጠሩ የተባረኩ ናቸው” ብለህ ጻፍ አለኝ፤ ቀጥሎም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው” አለ።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!


እግዚአብሔርን የሚፈሩና ትእዛዞቹን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው።


ስለ እኔ የማይጠራጠር የተባረከ ነው።”


ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃም፥ ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብ ጋር በመንግሥተ ሰማይ በማዕድ ይቀመጣሉ እላችኋለሁ።


ሲያስተምርም “እነሆ! የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” ይል ነበር።


ኢየሱስም፦ “መንግሥተ ሰማይ እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሉአቸው” አለ።


ስለዚህ አባቴ እኔን እንደ ሾመኝ እኔም እናንተን እሾማችኋለሁ።


በመንግሥቴም በማእድ ተቀምጣችሁ ትበላላችሁ፤ ትጠጣላችሁ፤ በዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።”


‘እኔ ሀብታም ነኝ፤ ብዙ ሀብት አለኝ፤ የሚጐድለኝ ምንም የለም’ ትላለህ፤ ነገር ግን ጐስቋላ፥ ምስኪን፥ ድኻ፥ ዕውርና የተራቈትህ መሆንክን አታውቅም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች