Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 3:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ስፍራ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የእፉኝት ልጆች! ከሚመጣው ቍጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ጥምቀት ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን አመለከታችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 3:7
49 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናንተ የእባብ ልጆች! ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ነገር መናገር እንዴት ትችላላችሁ? ሰው በአፉ የሚናገረው በልቡ ሞልቶ የተረፈውን ነው።


እንዲሁም እግዚአብሔር ከሞት ያስነሣውን፥ ከሚመጣው ቊጣ የሚያድነንን፥ የልጁን የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት እንዴት እንደምትጠባበቁም ይመሰክራሉ።


ሰዎች በክፋታቸው እውነት እንዳይታወቅ ያደርጋሉ፤ እግዚአብሔርንም ባለመፍራታቸውና በክፋታቸው ምክንያት በሁሉም ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ከሰማይ ይገለጣል።


እናንተ እባቦች፥ እባብ ልጆች፥ እንዴት ከገሃነም ቅጣት ማምለጥ ትችላላችሁ?


እንግዲህ የጸደቅነው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሆነ ይበልጡንም ከእግዚአብሔር ቊጣ የምንድነው በእርሱ አማካይነት ነው።


በዚያኑ ቀን፥ “የሙታን ትንሣኤ የለም” የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤


ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ልብ አድርጉ፤ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ” አላቸው።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፦ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም።


በዚያን ጊዜ በኢየሱስ አጠገብ የነበሩ ፈሪሳውያን ይህን ሰምተው “ታዲያ፥ እኛም ዕውሮች መሆናችን ነውን?” አሉት።


ከባቢሎን ሽሹ! ሕይወታችሁንም ለማትረፍ አምልጡ! ባቢሎን በሠራችው ኃጢአት ምክንያት በከንቱ አትለቁ! እኔ ለእርስዋ የሚገባትን ቅጣት በመስጠት የምበቀልበት ጊዜ ነው።


እኔም መልሼ እንዲህ አልኩ፦ “እኔ ብነግራቸውና ባስጠነቅቃቸው ማን ሊሰማኝ ይችላል? እነርሱ እልኸኞች ስለ ሆኑ፥ ቃልህን መስማት አይፈልጉም፤ የአንተን ቃል ስነግራቸው በንቀት መሳቂያ ያደርጉኛል።


ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።


ደግሞም ሊመሰክሩ ቢፈቅዱ ከሃይማኖታችን በጣም ወግ አጥባቂ ከሆነው ክፍል ፈሪሳዊ ሆኜ እንደ ኖርኩ ከመጀመሪያው አንሥቶ ያውቃሉ።


ስለዚህ እያንዳንዳችሁን ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን እንባዬን እያፈሰስኩ እንደ መከርኳችሁ እያስታወሳችሁ ተጠንቀቁ።


ነገር ግን ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ አማኞች ተነሡና “አሕዛብ እንዲገረዙና የኦሪትን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ ይገባል” አሉ።


የካህናት አለቃውና ከእርሱ ጋር የነበሩት የሰዱቃውያን ወገኖች ሁሉ በቅንነት ተሞልተው በእነርሱ ላይ ተነሡ፤


እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።


ሰዎቹ የተላኩት ከፈሪሳውያን ነበረ፤


“ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፥ ግፈኛ አመንዝራ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ ይልቁንም እንደዚህ እንደ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ።


ፈሪሳውያን ገንዘብ ወዳዶች ስለ ነበሩ፥ ኢየሱስ የተናገረውን ሁሉ ሰምተው አፌዙበት።


ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን በዮሐንስ እጅ አንጠመቅም በማለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ተቃውመው ነበር።


“የሙታን መነሣት የለም፤” የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ መጥተው፤ እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤


ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን በንግግሩ ለማጥመድ ወደ እርሱ ተላኩ።


ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠንቀቁ፤” ብሎ አዘዛቸው።


ኢየሱስ ሰዱቃውያንን መልስ አሳጥቶ ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ ፈሪሳውያን በአንድነት ተሰበሰቡ።


ከዚህ በኋላ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው ኢየሱስን በንግግሩ እንደሚያጠምዱት ተማከሩ፤


ፈሪሳውያን ግን ይህን በሰሙ ጊዜ “እርሱ ‘ብዔልዜቡል’ በተባለው በአጋንንት አለቃ አማካይነት ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም” አሉ።


ስለዚህ የእናንተ ጽድቅ ከሕግ መምህራንና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ ከቶ ወደ መንግሥተ ሰማይ እንደማትገቡ እነግራችኋለሁ።


እነርሱ የእባብ ዕንቊላል ይቀፈቅፋሉ፤ የሸረሪት ድርም ይፈትላሉ፤ እነዚያን ዕንቊላሎች የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤ ከሚቀፈቀፈው ዕንቊላል እፉኝት ይወጣል።


በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”


በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።


ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፦ “ፈሪሳውያን ይህን የተናገርከውን ሰምተው እንደ ተሰናከሉ ዐውቀሃልን?” ሲሉ ጠየቁት።


ሕግን የማያከብሩ ሰዎች ክፉ ሰዎችን ያመሰግናሉ፤ ሕግን የሚያከብሩ ግን ክፉዎችን ይቃወማሉ።


ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ መጡ፤ ሊፈትኑትም ፈልገው “ከሰማይ ተአምር አሳየን” ሲሉ ጠየቁት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች