Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 መንሹ በእጁ ነው፤ ዐውድማውን ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውን በጐተራ ይከትታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 መንሹ በእጁ ነው፤ አውድማውንም ያጠራል፤ ስንዴውን በጎተራ ይከተዋል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 3:12
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ገለባ በነፋስ የተወሰዱበት፥ እንደ ትቢያም በዐውሎ ነፋስ የተጠረጉበት ጊዜ አለን?


ክፉዎች ግን እንደዚህ አይደሉም፤ እነርሱ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው።


የእግዚአብሔር መልአክ ሲያሳድዳቸው፤ በነፋስ እንደሚበተን ገለባ ይሁኑ!


ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።


ሕዝቦች እንደ ኀይለኛ ውሃ ድምፅ ያሰማሉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲገሥጻቸው በተራራ ላይ ገለባዎች በነፋስ እንደሚበተኑና በዐውሎ ነፋስም ዐቧራ እንደሚበተን ርቀው ይሸሻሉ።


ዳግመኛ በወይን ቦታዬ ላይ አልቈጣም፤ የወይን ቦታዬን የሚያበላሹ ኲርንችትና እሾኽ ቢኖሩ ነቃቅዬ በእሳት በማቃጠል ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ።


ስንዴና ገብስ ይወቃሉ እንጂ እንዲደቁ አይደረጉም፤ ሠረገላና ፈረስ በላያቸው ላይ ቢነዱም እንኳ እንዲደቁ አይደረጉም።


የምታርሱባቸው በሬዎችና አህዮች በጨው የታሸ መኖና በመንሽና በአካፋ ተገለባብጦ የጠራውን ገፈራ ይመገባሉ።


ወደ ሰማይ ትበትናቸዋለህ፤ ነፋስም ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእኔ በእስራኤል ቅዱስም ትመካለህ።


የእስራኤል ቅዱስ የሠራዊት አምላክ ያዘዘውን ሕግና ያስተማረውን ሥርዓት ስለ አቃለሉ ገለባና ድርቆሽ በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ የእነርሱም ሥር መሠረት በስብሶ ይጠፋል፤ አበባቸውም ደርቆ እንደ ትቢያ ይበናል።


“ወጥተው ሲሄዱም በእኔ ላይ በማመፃቸው የተገደሉትን ሰዎች በድን ያያሉ፤ እነርሱን የሚበላቸው ትል አይሞትም፤ የሚያቃጥላቸውም እሳት አይጠፋም፤ እነርሱንም የሚያያቸው የሰው ዘር ሁሉ ይጸየፋቸዋል።”


ገለባ በነፋስ እንደሚበተን፥ በምድሪቱ ውስጥ ባሉት ከተሞች ሁሉ በተንኳችሁ፤ ከክፉ ሥራችሁም ካለመመለሳችሁ የተነሣ፥ እናንተን ሕዝቤን አጠፋኋችሁ፤ ልጆቻችሁ ሁሉ እንዲገደሉ አደረግሁ።


ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ”


በዚያን ጊዜ ለዚህ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ተብሎ ይነገራቸዋል፥ “በሕዝቤ ላይ የሚያቃጥል ነፋስ በበረሓ ካሉት ኰረብቶች ተነሥቶ ይነፍስባቸዋል፤ ይህም የሚያበጥር ወይም የሚያጠራ ነፋስ አይደለም።


እኔ እንደ እህል የሚያበጥሯትና ምድርዋን የሚያጠፉ የውጪ ጠላቶችን ወደ ባቢሎን እልካለሁ፤ እነርሱም የምትጠፉበት ጊዜ ሲደርስ ከየአቅጣጫው አደጋ ይጥሉባታል።


ስለዚህ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቤተ መቅደሴ በተሠራበት በዚህ ቦታ ላይ ብርቱ ቊጣዬን አፈሳለሁ፤ በሰዎችና በእንስሶች ላይ፥ በዛፎችና በሰብልም ሁሉ ላይ ሳይቀር አፈሰዋለሁ፤ ቊጣዬ ማንም ሊያጠፋው እንደማይችል እሳት ይሆናል።


በዚህም ምክንያት እነርሱ እንደ ማለዳ ጉም ተነው ይጠፋሉ፤ እንደ ጠዋት ጤዛም ይረግፋሉ፤ ከአውድማ ላይ በዐውሎ ነፋስ እንደሚጠረግ እብቅ ወይም በጢስ መውጫ ወጥቶ እንደሚያልቅ ጢስ ይሆናሉ።


“የእስራኤል ሕዝብ በሕዝቦች መካከል እንዲበተኑ አዛለሁ፤ የሚበተኑትም እህል በወንፊት እንደሚነፋ ዐይነት ነው፤ ነገር ግን ወንፊቱ ሲነቃነቅ ገለባው እንጂ አንድም ቅንጣት አይበተንም።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


ስለዚህ ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ስንዴውም እንክርዳዱም አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜ ዐጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳት እንዲቃጠልም በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን ሰብስቡና በጐተራዬ ክተቱ’ እላቸዋለሁ።”


በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ እነርሱም የኃጢአት ምክንያት የሆኑትንና ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ከእርሱ መንግሥት ሰብስበው ያወጣሉ፤


ወደ እቶን እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


ጻድቃን ግን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ፤ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”


ዮሐንስ ግን ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ሌላ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እኔ የእርሱን ጫማ ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የበቃሁ አይደለሁም፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።


እርሱ በአውድማ ላይ እህሉን ከገለባ ለመለየት መንሹን በእጁ ይዞአል፤ ካጣራውም በኋላ ጥሩውን እህል በጐተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ አባቴ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ግን አብዝቶ እንዲያፈራ ገርዞ ያጠራዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች