Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 25:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አምስት መክሊት የተቀበለው ወዲያውኑ ሄዶ ነገደበትና ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ዐምስት ታላንት የተቀበለው ሰው፣ ወዲያው በገንዘቡ ንግድ ጀምሮ ዐምስት ታላንት አተረፈ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አምስት መክሊት የተቀበለውም ሄዶ ነገደበትና ሌላ አምስት አተረፈ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት፤ ሌላም አምስት አተረፈ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 25:16
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉም በተሰበሰቡ ጊዜ ዳዊት ተነሥቶ፥ እንዲህ አለ፦ “ወገኖቼ ሆይ፥ አድምጡኝ፤ ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ ይሆን ዘንድ የተቀደሰው ታቦት የሚያርፍበት ቤት ለመሥራት ፈልጌ ነበር፤ ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ማሠሪያ የሚሆነውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅቼአለሁ፤


በንግድ የምታገኘውም ገንዘብ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ ለራስዋ ተቀማጭ ሳታደርግ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሚያስፈልጋቸው ምግብና በጥሩ ልብስ ያውሉታል።


ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል። የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂአለሽ፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ከቶ አያፍሩም።”


ንጉሡ መተሳሰብ በጀመረ ጊዜ በብዙ ሺህ መክሊት የሚቈጠር ዕዳ ያለበት አንድ አገልጋይ ተይዞ መጣ።


ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንዲሁ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ።


እርሱ ከመሄዱ በፊት ከአገልጋዮቹ ዐሥሩን ጠርቶ ለእያንዳንዱ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና ‘ተመልሼ እስክመጣ ድረስ በዚህ ገንዘብ ነግዱ’ አላቸው።


ነገር ግን ዳዊት በሕይወቱ ዘመን አገልግሎቱን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከፈጸመ በኋላ ሞቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮአል፤ መበስበስም ደርሶበታል።


ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።


በሥራ የሚደክም ገበሬ ከሥራው ከሚገኘው ፍሬ የመጀመሪያውን ማግኘት ይገባዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች