Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 24:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዚያን ጊዜ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን በመካድ ይሰናከላሉ፤ አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ሰዎችም እርስ በርሳቸው ይጣላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚያ ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ ይጠላላሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በዚያን ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጠላላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 24:10
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወላጆቻችሁና ወንድሞቻችሁ፥ ዘመዶቻችሁና ወዳጆቻችሁም ሳይቀሩ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ከእናንተ አንዳንዶቹ ይገደላሉ።


ወንድም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ በጠላትነት ይነሣሉ፤ ይገድሉአቸዋልም።


ስለ እኔ የማይጠራጠር የተባረከ ነው።”


ግን እነርሱ ለጊዜው ነው እንጂ በልባቸው ውስጥ ሥር አልሰደደም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በቃሉ ምክንያት ችግር ወይም ስደት ቢደርስባቸው ወዲያውኑ ተሰናክለው ይወድቃሉ።


በተከሰስኩበት ነገር የመጀመሪያ መከላከያዬን ባቀረብኩ ጊዜ ሁሉም ተለዩኝ እንጂ ከእኔ ጋር ሆኖ የረዳኝ ማንም አልነበረም፤ ይህንንም ነገር እግዚአብሔር እንደ በደል አድርጎ አይቊጠርባቸው።


ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በልቡ ውስጥ ሥር አልሰደደም፤ ስለዚህ በቃሉ ምክንያት አንዳች ችግር ወይም ስደት በደረሰበት ጊዜ ቶሎ ይሰናከላል።


ሰው የገዛ ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ እንዲሁም አባት የገዛ ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ በጠላትነት ይነሣሉ፤ ለሞትም አሳልፈው ይሰጡአቸዋል።


ዴማስ ይህን ዓለም ወዶ ተለይቶኛል፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፥ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


በእስያ ያሉት ሁሉ እኔን ትተውኝ እንደ ሄዱ ታውቃለህ፤ ከእነርሱም መካከል ፊጌሉስና ሄርሞጌኔስ ይገኛሉ።


በዚህም ምክንያት ተሰናክለውበት ሳይቀበሉት ቀሩ። ኢየሱስ ግን፦ “ነቢይ የማይከበረው በሀገሩና በገዛ ቤቱ ብቻ ነው” አላቸው።


ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች