Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 22:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘እነሆ፥ የሠርጉ ድግስ ተዘጋጅቶአል፤ የተጠሩት ግን ለግብዣው የተገቡ አልሆኑም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ከዚያም ባሮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘የሰርጉ ድግስ ዝግጁ ነው፤ ነገር ግን የተጋበዙት የሚገባቸው ሆነው ስላልተገኙ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በዚያን ጊዜ ባርያዎቹን እንዲህ አላቸው ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ የታደሙት ግን የተገቡ አልሆኑም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በዚያን ጊዜ ባሮቹን ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በዚያን ጊዜ ባሮቹን፦ ሰርጉስ ተዘጋጅቶአል፥ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 22:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ እነርሱ ነጭ ልብስ መልበስ የሚገባቸው ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።


ይህ ሁሉ ነገር የሚያሳየው የእግዚአብሔር ፍርድ ትክክል መሆኑንና እናንተንም መከራ ለተቀበላችሁለት መንግሥቱ ብቁ የሚያደርጋችሁ መሆኑን ነው።


ጳውሎስና በርናባስ ግን እንዲህ ሲሉ በድፍረት ተናገሩ፤ “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ እንዲነገር አስፈላጊ ነው፤ እናንተ አንቀበልም ካላችሁና የዘለዓለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን እነሆ፥ እኛ ዞር ብለን ወደ አሕዛብ እንሄዳለን።


ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ለመብላትና በደጃፎችዋም ወደ ከተማይቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን ያጠቡ የተባረኩ ናቸው።


ስለዚህ ከሚመጣው ክፉ ነገር ሁሉ ለማምለጥ ኀይል እንድታገኙና በሰው ልጅ ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ዘወትር ትጉ።”


ከሙታን ተነሥተው በሚመጣው ዓለም ለመኖር የተገባቸው ሰዎች ግን፥ አያገቡም፤ አይጋቡም።


እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ ሚዜዎች ማዘን ይገባቸዋልን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።


በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተቈጣና ወታደሮቹን ልኮ እነዚያን ገዳዮች አስገደለ፤ ከተማቸውንም በእሳት እንዲያቃጥሉ አደረገ፤


ስለዚህ በየአውራ ጐዳናው ሂዱና ያገኛችሁትን ሰው ሁሉ ወደ ሠርጉ ግብዣ ጥሩ።’


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች