Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 16:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በዚያን ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ፦ “አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስምዖን ጴጥሮስም፣ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” በማለት መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 16:16
38 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በጀልባውም ውስጥ የነበሩት ሁሉ “በእርግጥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” ብለው ለኢየሱስ ሰገዱለት።


እርስዋም “አዎ ጌታ ሆይ! አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው መሲሕ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አምናለሁ” አለችው።


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚያምን ሰው ውስጥ እግዚአብሔር ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።


የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውንም ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ!” አሉ።


እኛ ሰዎችን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን ሁሉ በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ የምናደርግ ስለ ሆነ በሥራ እንደክማለን፤ እንታገላለን።


ወዲያውም ሳውል በደማስቆ “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው” እያለ በየምኲራቡ ማስተማር ጀመረ።


ወደ እናንተ በመጣን ጊዜ እንዴት እንደ ተቀበላችሁን ሕያውና እውነተኛውን አምላክ ለማገልገል ከጣዖቶች ተለይታችሁ ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደ ተመለሳችሁ እነዚያ ሰዎች ራሳቸው ይመሰክራሉ።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ከሚያምን ሰው በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማነው?


ስለዚህ በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ እጅግ የሚያስፈራ ነው።


እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድስናው መንፈስ ከሞት በመነሣቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በታላቅ ኀይል ታወቀ።


“የእግዚአብሔርን ዐዋጅ ዐውጃለሁ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ፤


ኢየሱስ ግን ዝም አለ እንጂ ምንም መልስ አልሰጠም። የካህናት አለቃውም “የቡሩክ እግዚአብሔር ልጅ መሲሕ አንተ ነህን?” ሲል እንደገና ጠየቀው።


በመንግሥቴ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር በዐዋጅ አዝዤአለሁ፤ “እርሱ ሕያውና ዘለዓለማዊ አምላክ ነው፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤


ሕያው እግዚአብሔር በእሳት ውስጥ ሆኖ ከተናገረው በኋላ በሕይወት የኖረ ከሰው ዘር መካከል አንድ ሰው እንኳ ይገኛልን?


ነገር ግን ኢየሱስ መሲሕ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድታምኑና፥ አምናችሁም በእርሱ ስም የዘለዓለም ሕይወትን እንድታገኙ ይህ ተጽፎአል።


በዚህ ጊዜ ናትናኤል፥ “መምህር ሆይ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ! አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ!” አለ።


እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ ቀርባችኋል፤ እርስዋ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ናት፤ በደስታ ወደተሰበሰቡት፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት መላእክት ቀርባችኋል።


የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።


እናንተስ በእኛ አገልግሎት የመጣችሁ የክርስቶስ መልእክት መሆናችሁ ግልጥ ነው፤ ይህም መልእክት የተጻፈው በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፤ እንዲሁም በሰው ልብ ጽላት ላይ እንጂ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈ አይደለም።


“እናንተ ሰዎች ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እንደ እናንተ ሰዎች ነን፤ እኛ እዚህ የመጣነው እናንተ ከዚህ ከከንቱ ነገር ሁሉ ርቃችሁ ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሁሉ ወደ ፈጠረው ወደ ሕያው አምላክ እንድትመለሱ መልካም ዜና ልናበሥርላችሁ ነው፤


ፈታኙ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ፥ እስቲ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው።


ሕያው አምላክ ሆይ! ውሃ የመጠማትን ያኽል አንተን እናፍቃለሁ፤ ፊትህን ለማየት ወደ አንተ የምመጣው መቼ ነው?


ሲሄዱም ውሃ ወዳለበት ቦታ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “እነሆ፥ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ነገር ምንድን ነው?” አለ። [


እኛስ አምነናል፤ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ አንተ እንደ ሆንክም ዐውቀናል።”


ያዕቆብ መሲሕ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያም እጮኛ የሆነውን ዮሴፍን ወለደ።


ኢየሱስም “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው።


እነሆ! ዛሬ በዳዊት ከተማ አዳኝ ተወልዶላችኋል፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።


ሕያው አብ እንደ ላከኝና እኔም በእርሱ ሕያው እንደ ሆንኩ እንዲሁም ሥጋዬን የሚበላ ሁሉ በእኔ ሕያው ይሆናል።


በዚህ ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ።


እኔና ሲላስ፥ ጢሞቴዎስም የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን የሰበክንላችሁ ሁልጊዜ “አዎን” በሚል ቃል ብቻ እንጂ፥ “አዎን ወይም አይደለም” በሚል አወላዋይ ቃል አልነበረም።


ወዳጆቼ ሆይ፥ ከእናንተ መካከል ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያርቅ ክፉና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።


በዘለዓለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር የሌለበት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድናገለግል ኅሊናችንን ከሞተ ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን!


የሕያው አምላክን ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክም ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤ ምድርንና ባሕርን እንዲጐዱ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት ድምፁን ከፍ አድርጎ፥


ፊልጶስም “በሙሉ ልብህ ካመንክ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምናለሁ” አለ።]


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች