Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 13:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሌላው ዘር ብዙ ዐፈር በሌለበት በጭንጫማ መሬት ላይ ወደቀ፤ መሬቱም ብዙ ዐፈር ስለሌለበት ጥልቀት አልነበረውም፤ ስለዚህ ዘሩ ወዲያውኑ በቀለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አንዳንዱም ዘር በቂ ዐፈር በሌለበት በድንጋያማ መሬት ላይ ወደቀ፤ ዐፈሩ ጥልቀት ስላልነበረው ፈጥኖ በቀለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አንዳንዱም ብዙ አፈር በሌለበት በጭንጫማ መሬት ላይ ወደቀ፤ መሬቱም ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀ፤ ጥልቅ መሬትም ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀ፤ ጥልቅ መሬትም ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 13:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ አዲስ መንፈስንም በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ከሰውነታቸው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣቸዋለሁ።


አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ ከሰውነታችሁ እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣችኋለሁ።


ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።


ልባቸውንም እንደ አለት ድንጋይ አጠነከሩ፤ ጥንት በነበሩት ነቢያት አማካይነት እኔ የሠራዊት አምላክ በመንፈሴ የሰጠኋቸውን ሕግ ሁሉ በእልኸኛነት የማያዳምጡ ሆኑ፤ ስለዚህ እኔ የሠራዊት አምላክ ኀይለኛ ቊጣ አወረድኩባቸው።


በጭንጫማ መሬት ላይ የተዘራው የሚያመለክተው፥ ቃሉን ሰምቶ ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበለውን ሰው ነው።


ሲዘራም አንዳንዱ ዘር በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት።


ይሁን እንጂ ፀሐይ በወጣ ጊዜ ጠወለገ፤ ሥር ስላልነበረውም ደረቀ።


እንዲሁም በጭንጫማ ቦታ ላይ የተዘራው የሚያመለክተው ቃሉን ሲሰሙ ወዲያው በደስታ የሚቀበሉትን ሰዎች ነው፤


ሌላው ዘር ብዙ ዐፈር በሌለበት በጭንጫማ ቦታ ላይ ወደቀ፤ ቦታውም ብዙ ዐፈር ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች