Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 13:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ጻድቃን ግን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ፤ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 በዚያ ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሓይ ያበራሉ። ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 13:43
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ጊዜ ጠቢባን እንደ ሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃሉ፤ ብዙ ሰዎችን በማስተማር ከክፉ መንገድ ወደ ደግ ሥራ የመለሱ ሁሉ ለዘለዓለም እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበራሉ።”


“እናንተ እንደ ታናናሽ መንጋ የሆናችሁ ወገኖቼ አትፍሩ፤ የሰማይ አባታችሁ መንግሥትን ሊሰጣችሁ ፈቅዶአል።


የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!


በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።


ስለዚህ አባቴ እኔን እንደ ሾመኝ እኔም እናንተን እሾማችኋለሁ።


በአባቴ መንግሥት አዲሱን የወይን ፍሬ ጭማቂ ከእናንተ ጋር እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ ከዚህ የወይን ፍሬ ጭማቂ ዳግመኛ አልጠጣም እላችኋለሁ፤”


ታርዤ ነበር፥ አልብሳችሁኛል፤ ታምሜ ነበር፥ ጠይቃችሁኛል፤ ታስሬ ነበር መጥታችሁ ጐብኝታችሁኛል።’


እንግዲህ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”


እነርሱም ፊቱ ሲያበራ ያዩት ነበር፤ ስለዚህም ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደዚያ እስከሚሄድበት ጊዜ ድረስ ፊቱን በሻሽ ይሸፍን ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች