Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 10:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የዐሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ዝርዝር፥ እንደሚከተለው ነው፦ መጀመሪያ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፥ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስም የሚከተለው ነው፤ መጀመሪያ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የዐሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የዐሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 10:2
44 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን፥ ያዕቆብንና የያዕቆብን ወንድም ዮሐንስን ብቻ አስከትሎ፥ ለብቻው ወደ አንድ ከፍተኛ ተራራ ላይ ወጣ።


ከዚህ በኋላ የዘብዴዎስ ልጆች እናት፥ ከልጆችዋ ጋር ወደ ኢየሱስ ቀረበችና በፊቱም ተንበርክካ አንድ ነገር እንዲያደርግላት ለመነችው።


ከእርሱ ጋር ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስን ልጆች አስከትሎ ሄደ፤ ያዝንና ይጨነቅም ጀመረ።


ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፥ ዓሣ አጥማጆች የነበሩትን ሁለት ወንድማማች እነርሱም ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንንና ወንድሙን እንድርያስን፥ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ።


ከዚያም እልፍ ብሎ፥ የዘብዴዎስ ልጆች የሆኑትን ሌሎች ሁለት ወንድማማች ያዕቆብንና ዮሐንስን አየ። እነርሱም ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ላይ ሆነው መረባቸውን ሲጠግኑ ሳለ ጠራቸው።


በዚያኑ ጊዜ ኢየሱስ ከምኲራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት ገባ።


ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፥ ያዕቆብ፥ ዮሐንስና፥ እንድርያስ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው


ሐዋርያት ከተላኩበት ተመልሰው መጥተው በኢየሱስ ፊት ተሰበሰቡ፤ ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት።


በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ ትላለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ አንዳንዶችን ይገድላሉ፤ የቀሩትንም ያሳድዳሉ፤


የእራት ሰዓት በደረሰ ጊዜ ኢየሱስ ከሐዋርያት ጋር በማእድ ተቀመጠ።


ኢየሱስ “የፋሲካውን ራት እንድንበላ ሄዳችሁ አዘጋጁልን” ሲል ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው።


እንዲሁም የስምዖን ጓደኞች የሆኑት የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተገርመው ነበር። ኢየሱስ ስምዖንን፦ “አይዞህ አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው።


ሐዋርያት ከተላኩበት ተመልሰው መጡና ያደረጉትን ሁሉ ለኢየሱስ ነገሩት። እርሱም በቤተ ሳይዳ ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው ገለልተኛ ቦታ ብቻቸውን ይዞአቸው ሄደ።


ፊልጶስም ሄዶ ለእንድርያስ ነገረው፤ እንድርያስና ፊልጶስ አብረው ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት።


ኢየሱስ ይወደው የነበረው፥ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ጐን ተቀምጦ ነበር።


ስለዚህ እርስዋ ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ወደሚወደው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር እየሮጠች ሄደችና “ጌታን ከመቃብሩ አውጥተው ወስደውታል፤ የት እንዳኖሩት አናውቅም” አለቻቸው።


ስምዖን ጴጥሮስ፥ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ፥ የቃና ዘገሊላው ናትናኤል፥ የዘብዴዎስ ልጆችና ሌሎች ሁለት ደቀ መዛሙርት አብረው ነበሩ።


ጴጥሮስ ዘወር ብሎ ኢየሱስ የሚወድደው ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር በእራት ጊዜ ወደ ኢየሱስ ተጠግቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው።


ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ የመሰከረና እነዚህንም ነገሮች የጻፈ ይህ ደቀ መዝሙር ነው፤ የእርሱም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ እናውቃለን።


ስለዚህ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት፥ “እናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁን?” አላቸው።


ኢየሱስም “እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጬአችሁ የለምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው” አላቸው።


ይህንንም ያለው ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮታዊው ይሁዳ ነበር፤ ይሁዳ ምንም እንኳ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆን ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ስለ ነበር ነው።


ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ እንዲህ አለ፦


ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ወደሚኖሩበት ሰገነት ላይ ወጡ፤ እነርሱም “ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ በርተሎሜዎስ፥ ማቴዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ” ናቸው።


ዕጣም በጣሉ ጊዜ ዕጣው ለማትያስ ወጣ፤ ስለዚህ እርሱ ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።


የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ አስገደለው።


አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፤


ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ታየ፤ ለሐዋርያትም ሁሉ ታያቸው።


እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው።


ስለዚህ ለሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ የተቀደሳችሁ ምእመናን ሆይ! የእምነታችን ሐዋርያና የካህናት አለቃ ኢየሱስን አስቡ።


የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጴጥሮስ፥ መጻተኞች ሆናችሁ በጳንጦስ፥ በገላትያ፥ በቀጰዶቅያ፥ በእስያ፥ በቢታንያ ተበታትናችሁ ለምትኖሩት


የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤


ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆችዋ፤ ከእኔ ከሽማግሌው የተላከ መልእክት፤ እኔ በእውነት እወዳችኋለሁ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ይወዱአችኋል፤


በእውነት ለማፈቅረው፥ ለተወደደው ጋይዮስ፥ ከእኔ ከሽማግሌው የተላከ መልእክት፦


ይህ ራእይ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚሆነውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ይህን ራእይ ገለጠለት።


በኢየሱስ ክርስቶስ የመከራውና የመንግሥቱ እንዲሁ የትዕግሥቱ ከእናንተ ጋር ተካፋይ የሆንኩ እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ታስሬ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርኩ፤


ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!


እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ፤ እነዚህን ነገሮች በሰማሁና ባየሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ልሰግድለት በእግሩ ሥር ወደቅኩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች