Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 7:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተም ደግሞ ይህን አታስተውሉምን? ከውጪ ወደ ሰው የሚገባ ነገር ሰውን ምንም እንደማያረክሰው አይገባችሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እርሱም፣ “እናንተም አይገባችሁምን? ከውጭ ወደ ሰው ገብቶ ሊያረክሰው የሚችል አንዳች ነገር የለም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እርሱም፥ “እናንተም ነገሩ አይገባችሁምን? ከውጭ ወደ ሰው ገብቶ ሊያረክሰው የሚችል አንዳች ነገር የለም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እርሱም “እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሱም፦ እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 7:18
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰውን የሚያረክሰው ከአፍ የሚወጣው ነው እንጂ ወደ አፍ የሚገባው አይደለም!”


እንግዲህ ‘ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ!’ ብዬ ስነግራችሁ ስለ እንጀራ አለመሆኑን እንዴት አታስተውሉም?”


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተም ይህ ምሳሌ አይገባችሁምን? ታዲያ፥ ሌሎችን ምሳሌዎች ሁሉ እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ?


ኢየሱስ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ ምሳሌው ጠየቁት።


በሆድ በኩል ተላልፎ ወደ ውጪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይሄድም፤”። በዚህም ኢየሱስ ምግብ ሁሉ ንጹሕ መሆኑን ገለጸ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታስተውሉና ነቢያት የተናገሩትንም ሁሉ ከማመን ልባችሁ የዘገየ!


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ይህን አታውቅምን?


ጠንካራ ምግብ መብላት እንደማይችሉ ሕፃናት ስለ ሆናችሁ እኔ የመገብኳችሁ ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም፤ አሁንም ቢሆን ጠንካራ ምግብ መመገብ ገና የማትችሉ ናችሁ።


ስለዚህ ጉዳይ የምንናገረው ብዙ ነገር አለ፤ ነገር ግን የማስተዋል ችሎታችሁ አነስተኛ ስለ ሆነ ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች