Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 4:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ያለ ምሳሌም አያስተምራቸውም ነበር፤ ብቻቸውን ሲሆኑ ግን ሁሉን ነገር ለደቀ መዛሙርቱ ያስረዳቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ምንም ነገር ያለ ምሳሌ አይነግራቸውም ነበር። እርሱና ደቀ መዛሙርቱ ብቻ በሚሆኑበት ጊዜ ግን ሁሉንም ነገር በዝርዝር ያስረዳቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀመዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 4:34
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስ ይህን ሁሉ ነገር በምሳሌ ለሕዝቡ ተናገረ፤ ያለ ምሳሌም ምንም ነገር አልተናገራቸውም።


ኢየሱስ ብቻውን በሆነ ጊዜ ይከተሉት የነበሩ ሰዎችና ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ስለ ምሳሌዎቹ ትርጒም ጠየቁት።


ኢየሱስም ሰዎች ማስተዋል በሚችሉበት መጠን፥ እነዚህን በመሳሰሉ ብዙ ምሳሌዎች ቃሉን ይነግራቸው ነበር።


ከዚህ በኋላ ከሙሴና ከነቢያት መጻሕፍት ጀምሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተነገረውን እየጠቀሰ አስረዳቸው።


ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የተናገረውን አላስተዋሉም።


“እስከ አሁን በምሳሌ ነገርኳችሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ በምሳሌ የማልናገርበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ስለ አብ ሁሉን ነገር ገልጬ እነግራችኋለሁ።


ቀን ከቀጠሩለትም በኋላ ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ፤ እርሱም ከጧት እስከ ማታ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በመመስከር አሳቡን ገለጠላቸው፤ እነርሱንም ለማሳመን ከሙሴ ሕግና ከነቢያት መጻሕፍት እየጠቀሰም ስለ ኢየሱስ አስረዳቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች