Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሽባውም ወዲያውኑ ተነሣና አልጋውን ተሸክሞ በሰዎቹ ሁሉ ፊት ወጣ። ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አይተን አናውቅም እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እርሱም ተነሥቶ ሁሉም እያዩት ዐልጋውን ተሸክሞ ሄደ፤ በስፍራው የነበሩትም ሁሉ በሁኔታው በመደነቅ፣ “የዚህ ዐይነት ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም!” በማለት ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እርሱም ተነሥቶ ሁሉም እያዩት ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ ሄደ፤ ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው “እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም፤” እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፤ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና “እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም፤” ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፥ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና፦ እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 2:12
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡም ሁሉ ተገርመው፥ “ይህ የዳዊት ልጅ ይሆንን?” አሉ።


ስለዚህ ሕዝቡ ድዳዎች ሲናገሩ፥ ሽባዎች ሲድኑ፥ አንካሳዎች በደኅና ሲራመዱ፥ ዕውሮች ሲያዩ በተመለከቱ ጊዜ ተደንቀው የእስራኤልን አምላክ አመሰገኑ።


ጋኔኑም ከእርሱ በወጣ ጊዜ ድዳው ሰው ተናገረ፤ ሕዝቡም “እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ከቶ ታይቶ አይታወቅም!” እያሉ ተደነቁ።


ሕዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ ተገረሙ፤ እንዲህ ያለውንም ሥልጣን ለሰው በመስጠቱ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


“ይህ ምንድን ነው? ምን ዐይነት አዲስ ትምህርት ነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳ በሥልጣኑ ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤” እያሉ ሁሉም በመገረም እርስ በርሳቸው ይጠያየቁ ጀመር።


“ተነሥ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ እልሃለሁ” አለው።


እጆቹን ጫነባት፤ ወዲያውም ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።


ከእነርሱም አንዱ ከለምጹ መንጻቱን ባየ ጊዜ በከፍተኛ ድምፅ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ተመለሰ።


በዚያም የነበሩ ሰዎች ሁሉ እጅግ ተገርመው፥ በመፍራት፥ “ዛሬ ድንቅ ነገር አየን፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


ሁሉንም ፍርሀት ይዞአቸው፥ “ታላቅ ነቢይ ከመካከላችን ተነሥቶአል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያድን መጥቶአል፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


ሆኖም ከሕዝቡ ብዙዎቹ በእርሱ አመኑ፤ እንዲህም አሉ፦ “መሲሕ በሚመጣበትስ ጊዜ ይህ ሰው ካደረጋቸው ተአምራት የበለጠ ያደርጋልን?”


ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ዐይኖች ያበራ አለ ሲባል ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ተሰምቶ አይታወቅም።


የሕዝብ አለቆችና የሸንጎው አባሎች ጴጥሮስንና ዮሐንስን የሚያስቀጣ ምንም ምክንያት ባለማግኘታቸው፥ ሕዝቡንም ስለ ፈሩ እንደገና አስጠንቅቀው ለቀቁአቸው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያመሰግን ስለ ነበር ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች