Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 8:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 ኢየሱስ ገና ይህንን በመናገር ላይ ሳለ አንድ ሰው ከምኲራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን በከንቱ አታድክመው!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ፣ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታድክመው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 እርሱም ይህን እየተናገረ ሳለ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ “ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 ይህ​ንም ሲና​ገር አንድ ሰው ከም​ኵ​ራቡ ሹም ቤት መጥቶ፥ “ልጅ​ህስ ሞታ​ለች እን​ግ​ዲህ መም​ህ​ሩን አታ​ድ​ክ​መው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 እርሱም ገና ሲናገር አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ቤት መጥቶ፦ ልጅህ ሞታለች፤ እንግዲህ መምህሩን አታድክም አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 8:49
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ የመቶ አለቃው ወዳጆቹን እንዲህ ሲል ወደ ኢየሱስ ላከ፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ወደ ቤቴ ትገባ ዘንድ ያልተገባሁ ነኝና ወደ ቤቴ ለመምጣት አትድከም።


አካዝ ግን “ምልክት ስጠኝ ብዬ አልጠይቅም፤ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም” አለ።


ታዲያ፥ ያ ወዳጁ ከውስጥ ሆኖ፥ ‘እባክህ አታስቸግረኝ! በሩ ተቈልፎአል፤ ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል፤ ስለዚህ ተነሥቼ የፈለግኸውን እንጀራ ልሰጥህ አልችልም፤’ ይለዋልን?


ኢየሱስ ይህን ሲነግራቸው ሳለ፥ አንድ የምኲራብ አለቃ ወደ እርሱ መጣ፤ በግንባሩም በኢየሱስ ፊት ተደፍቶ፥ “እነሆ፥ ልጄ አሁን ሞተችብኝ፤ ነገር ግን አንተ መጥተህ እጅህን ብትጭንባት ትድናለች” አለው።


ኢየሱስም ይህን ማለታቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “ይህችን ሴት ለምን ታስቸግሩአታላችሁ? እርስዋ ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች፤


እዚያም ከምኲራብ አለቆች አንዱ የነበረ፥ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው ኢየሱስን ባየው ጊዜ በእግሩ ሥር ወድቆ


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች