Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 7:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ይህን በሰሙ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቀራጮችም እንኳ ሳይቀሩ በዮሐንስ እጅ ተጠምቀው ስለ ነበር የእግዚአብሔር ሥራ ትክክል መሆኑን ተገነዘቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ቀረጥ ሰብሳቢዎች እንኳ ሳይቀሩ፣ ይህን የሰሙ ሁሉ፣ የዮሐንስን ጥምቀት በመጠመቅ ለእግዚአብሔር ተገቢውን ክብር ሰጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የሰማውም ሕዝብ ሁሉ፥ ቀራጮች እንኳ ሳይቀሩ፥ በዮሐንስ ጥምቀት በመጠመቃቸው የእግዚአብሔርን ጻዲቅነት ተቀበሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ሕዝ​ቡም ሁሉ ቀራ​ጮ​ችም በሰሙ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጻድቅ ነው አሉት፤ የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ተጠ​ም​ቀው ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የሰሙትም ሕዝብ ሁሉ ቀራጮች እንኳ ሳይቀሩ በዮሐንስ ጥምቀት ተጠምቀው እግዚአብሔርን አጸደቁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 7:29
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቀራጮችም ሊጠመቁ ወደ እርሱ መጥተው “መምህር ሆይ! እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ጠየቁት።


የጥበብ ትክክለኛነት በልጆችዋ ይረጋገጣል።”


በውሃ ላይ ሥልጣን ያለው መልአክ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ያለህና የነበርክ ቅዱስ ጌታ ሆይ! እንዲህ ስለ ፈረድክ አንተ ትክክለኛ ነህ፤


የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤


እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያጸድቅበትን መንገድ ባለማወቃቸው የራሳቸውን የጽድቅ መንገድ ተከተሉ እንጂ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አልተከተሉም።


ጳውሎስም “ታዲያ፥ ምን ዐይነት ጥምቀት ነው የተጠመቃችሁት?” አላቸው። እነርሱም “የዮሐንስን ጥምቀት ነው” አሉት።


ስለ ጌታ መንገድ የተማረና በመንፈስም የተቃጠለ ሆኖ ስለ ኢየሱስ በትክክል ይሰብክና ያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ እርሱ የሚያውቀው የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ ነበር።


እኔ ያመፅኩት በአንተ ላይ ነው፤ የበደልኩትም አንተን ብቻ ነው፤ አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው።


አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።


የሚወዱአችሁን ሰዎች ብቻ ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ኃጢአተኞችስ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?


ሴቶች ከወለዱአቸው ሰዎች መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።”


‘ከሰው ነው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉም በዮሐንስ ነቢይነት ስለሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች