Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 7:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የኢየሱስ ዝና በይሁዳ ምድር ሁሉና በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ይህም የኢየሱስ ዝና በመላው ይሁዳና በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ስለ እርሱም የተነገረው ይህ ነገር በመላው ይሁዳ በዙሪያውም ባለው አገር ሁሉ ተሰራጨ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ይህም የእ​ርሱ ዜና በይ​ሁዳ ሀገ​ሮች ሁሉና በአ​ው​ራ​ጃዋ ሁሉ ተሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ይህም ዝና ስለ እርሱ በይሁዳ ሁሉ በዙሪያውም ባለች አገር ሁሉ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 7:17
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደፊት ራመድ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ ቃሬዛውንም የተሸከሙት ሰዎች ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ!” አለ።


የኢየሱስ ዝና በሁሉም ዘንድ ስለ ታወቀ፥ ንጉሡ ሄሮድስ ስለ እርሱ ሰማ። አንዳንድ ሰዎች፥ “መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶአል፤ ስለዚህ ይህ ሁሉ ተአምራት በእርሱ ይደረጋል” ይሉ ነበር።


ወዲያውኑ፥ የኢየሱስ ዝና በገሊላ ዙሪያ ባሉት አገሮች ሁሉ ተሰማ።


እነርሱ ግን ሄደው በዚያ አገር ሁሉ ስለ ኢየሱስ ዝና አወሩ።


የዚህም ነገር ዝና በዚያ አገር ሁሉ ተሰማ።


ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።


በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን፥ በይሁዳ ምድር በምትገኝ በቤተልሔም ከተማ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


ኢየሱስም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተሞልቶ ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት አካባቢዎች ሁሉ ተሰማ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች