Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 5:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ለመሆኑ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል፥’ ከማለትና ‘ተነሥተህ ሂድ!’ ከማለት የትኛው ይቀላል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ‘ኀጢአትህ ተሰረየልህ’ ከማለትና ‘ተነሥተህ ሂድ’ ከማለት የትኛው ይቀልላል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ‘ኀጢአቶችህ ተሰረዩልህ፤’ ከማለትና ‘ተነሣና ሂድ፤’ ከማለት የትኛው ይቀላል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ኀጢ​አ​ትህ ተሰ​ረ​የ​ልህ ከማ​ለ​ትና ተነ​ሥ​ተህ ሂድ ከማ​ለት ማና​ቸው ይቀ​ላል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 5:23
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሽባውን፥ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል፤’ ከማለትና፥ ‘ተነሥተህ አልጋህን ተሸከምና ሂድ!’ ከማለት የትኛው ይቀላል?


ለመሆኑ ‘ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል’ ከማለትና ‘ተነሥተህ ሂድ!’ ከማለት የትኛው ይቀላል?


በዚያም ሰዎች በአልጋ ላይ የተኛ አንድ ሽባ ይዘው ወደ እርሱ መጡ። እርሱም እምነታቸውን አይቶ፥ ሽባውን፥ “ልጄ ሆይ! አይዞህ፤ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።


ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “በልባችሁ ስለምን ይህን ታስባላችሁ?


ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ለመደምሰስ ሥልጣን እንዳለው ማወቅ አለባችሁ” ብሎ ሽባውን ሰው፦ “አንተ ሰው ተነሥ፤ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ!” አለው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሴትዮዋን፥ “ኃጢአትሽ ይቅር ተብሎልሻል፤” አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች