Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 22:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ጽዋውን አንሥቶ ከአመሰገነ በኋላ እንዲህ አለ፦ “እንካችሁ ይህንን ተካፈሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ጽዋውን ተቀብሎ ካመሰገነ በኋላ እንዲህ አላቸው፤ “ዕንካችሁ፤ ሁላችሁ ከዚህ ተካፈሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጽዋንም ተቀበሎ፥ አመስግኖም “እንካችሁ፤ ይህን በመካከላችሁ ተካፈሉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ጽዋ​ው​ንም ተቀ​ብሎ አመ​ሰ​ገነ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህን እንኩ ሁላ​ች​ሁም ተካ​ፈ​ሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ጽዋንም ተቀበለ አመስግኖም፦ ይህን እንካችሁ በመካከላችሁም ተካፈሉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 22:17
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቀጥሎም ኢየሱስ ኅብስት አንሥቶ ከአመሰገነ በኋላ፤ ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ “እንካችሁ፤ ይህ ለእናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሎ ሰጣቸው።


እግዚአብሔር ስላዳነኝ አመሰግነዋለሁ፤ የወይን ጠጅ መባም አቀርብለታለሁ።


አንዱን ቀን ከሌላው ቀን አስበልጦ የሚያከብር ቢኖር ይህን ማድረጉ ለጌታ ክብር ብሎ ነው፤ ማንኛውንም ምግብ የሚበላ ለጌታ ክብር ብሎ ይበላል፤ ስለሚበላውም ምግብ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤ ማንኛውንም ምግብ የማይበላ ለጌታ ክብር ብሎ አይበላም፤ ባለመብላቱም እግዚአብሔርን ያመሰግናል።


ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ቈርሶም ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤


ወዳጁ የሞተበትን ሰው ለማጽናናት የእዝን እንጀራ በመውሰድ አብሮት የሚበላና የሚጠጣ አይኖርም፤ ሌላው ቀርቶ እናትም አባትም የሞቱበትን የሚያጽናና አይገኝም።


በልተህ ትጠግባለህ፤ ይህችን ለም ምድር የሰጠህን እግዚአብሔር አምላክህንም ታመሰግናለህ።


በጠላቶቼ ፊት ታላቅ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ትቀባልኛለህ፤ ጽዋዬም እስኪትረፈረፍ ድረስ ይሞላል።


ወደ ከተማው እንደ ገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ፤ መሥዋዕቱን መባረክ ስላለበት ሕዝቡ እርሱ ከመምጣቱ በፊት አይበሉም፤ ከዚያም በኋላ ተጋባዦቹ ይበላሉ፤ ፈጥናችሁ ውጡ፤ አሁን ታገኙታላችሁ” አሉአቸው።


ከዚህ በኋላ ሕዝቡ በመስኩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ አንሥቶ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና የምስጋና ጸሎት አደረገ፤ እንጀራውንም ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ዐደሉ።


ሰባቱን እንጀራና ዓሣውንም አንሥቶ የምስጋና ጸሎት አደረገ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ዐደሉ።


ሲበሉም ኢየሱስ ኅብስት አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ “እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው” ብሎ ሰጣቸው።


እነርሱ በመብላት ላይ ሳሉ ኢየሱስ ኅብስት አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ “እንካችሁ፥ ይህ ሥጋዬ ነው” ብሎ ሰጣቸው።


እኛ እግዚአብሔርን አመስግነን የምንካፈለው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰው ኅብስት ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?


ከጌታ የተቀበልኩትና ለእናንተም ያስተላለፍኩላችሁ ትምህርት ይህ ነው፤ ጌታ አልፎ በተሰጠበት ሌሊት ኅብስት አነሣ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች