Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 22:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የቤቱንም ጌታ መምህራችን፥ ‘ከደቀ መዛሙርቴ ጋር የፋሲካን ራት የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ ቤት የት ነው? ይልሃል’ በሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ለቤቱም ባለቤት፣ ‘መምህሩ፣ ከደቀ መዛሙርቴ ጋራ የፋሲካን እራት የምበላበት የእንግዳ ክፍል ወዴት ነው? ይልሃል’ በሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ለባለቤቱም ‘መምህሩ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ክፍል የት ነው?’ ይልሃል በሉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የዚ​ያን ቤት ጌታ፦ መም​ህር ከደቀ መዛ​ሙ​ርቴ ጋር የፋ​ሲ​ካን በግ የም​በ​ላ​በት ቤት ወዴት ነው? ብሎ​ሃል በሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ለባለቤቱም፦ መምህሩ፦ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ክፍል ወዴት ነው? ይልሃል በሉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 22:11
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ማንም ሰው አንዳች ነገር ቢላችሁ ‘ጌታ ስለሚፈልጋቸው ነው’ በሉት። እርሱም አህዮቹን ወዲያውኑ ይልካቸዋል።”


ወደሚገባበትም ቤት ሂዱና የቤቱን ጌታ፥ ‘መምህር፥ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር የፋሲካን ራት የምበላበት ለእኔ የሚሆን የእንግዳ ማረፊያ ቤት የት ነው?’ ይላል በሉት።


ማንም ሰው ‘ለምን ትፈቱታላችሁ?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ ‘ጌታ ስለሚያስፈልገው ነው’ ብላችሁ መልሱለት።”


እነርሱም “ለጌታ ስለሚያስፈልገው ነው” አሉ።


ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ ቀና ብሎ ተመለከተና ዘኬዎስን፥ “ዘኬዎስ ሆይ! ዛሬ በአንተ ቤት መዋል ይገባኛልና ፈጥነህ ከዛፉ ውረድ” አለው።


እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ከተማ ስትገቡ እነሆ፥ የውሃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ፤ እርሱን ተከትላችሁ ወደሚገባበት ቤት ሂዱ።


እርሱም በሰገነት ላይ ያለውን ተነጥፎ የተዘጋጀ ሰፊ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁ።”


ማርታ ይህን ከተናገረች በኋላ ሄደችና እኅትዋን ማርያምን “መምህር መጥቶአል፤ አንቺንም ይጠራሻል” ብላ በስውር ጠራቻት።


እነሆ! እኔ በበር ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ ገብቼ ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች