Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 21:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ወላጆቻችሁና ወንድሞቻችሁ፥ ዘመዶቻችሁና ወዳጆቻችሁም ሳይቀሩ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ከእናንተ አንዳንዶቹ ይገደላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ወላጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁና ጓደኞቻችሁ እንኳ ሳይቀሩ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ከእናንተም አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወላጆችና ወንድሞች፥ ዘመዶችና ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወላ​ጆ​ቻ​ች​ሁና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ ወዳ​ጆ​ቻ​ች​ሁና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 21:16
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባት በልጁ ላይ፥ ልጅም በአባቱ ላይ፥ እናት በሴት ልጅዋ ላይ፥ ሴት ልጅም በእናትዋ ላይ፥ ዐማት በምራትዋ ላይ፥ ምራትም በዐማትዋ ላይ በመነሣት ይለያያሉ።”


አምስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ሰጡትም ምስክርነት የተገደሉትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ፤


እያንዳንዱ ከባልንጀራው ተንኰል ይጠንቀቅ፤ ወንድሙን እንኳ ቢሆን ማመን የለበትም፤ ወንድም የተባለ ሁሉ (እንደ ያዕቆብ) አታላይ ሆኖአል፤ ወዳጅ የተባለም ሁሉ የባልንጀራውን ስም ያጠፋል።


እነርሱ በበጉ ደምና በተናገሩት የምስክርነት ቃል ድል ነሥተውታል፤ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋል፤


አንተ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ስፍራ መኖርህን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል፤ በእኔ ላይ ያለህን እምነት አልካድክም፤ ታማኝ ምስክሬ የነበረው አንቲጳስ ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ ከተማ በተገደለ ጊዜ እንኳ በእኔ ማመንህን አልተውክም።


የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ አስገደለው።


በድንጋይ ሲወግሩት ሳሉ እስጢፋኖስ፥ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ! ነፍሴን ተቀበል!” ብሎ ጸለየ።


ወንድም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ በጠላትነት ይነሣሉ፤ ይገድሉአቸዋልም።


ሰው የገዛ ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ እንዲሁም አባት የገዛ ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ በጠላትነት ይነሣሉ፤ ለሞትም አሳልፈው ይሰጡአቸዋል።


ወንድሞችህና የቅርብ ዘመዶችህ ከድተውሃል፤ በአንተ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፤ ስለዚህ በፊትህ ስለ አንተ መልካም ነገር ቢናገሩም አትመናቸው።”


ከጠላቶቻችሁ ማንም ሊቋቋመው ወይም ሊቃወመው የማይችለውን አንደበትና ጥበብ እኔ እሰጣችኋለሁ።


ስለ ስሜም በሰው ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች