Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 2:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ከመንገደኞች ጋር አብሮ የሚሄድ መስሎአቸው የአንድ ቀን መንገድ ሲጓዙ ዋሉ፤ ከዚያም በኋላ ከዘመዶቻቸውና ከሚያውቋቸው ሰዎች ዘንድ ይፈልጉት ጀመር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 ዐብሯቸው ያለ መስሏቸው የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላ ግን ከዘመዶቻቸውና ከወዳጆቻቸው ዘንድ ይፈልጉት ጀመር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ነገር ግን ከመንገደኞች ጋር የነበረ መስሏቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፤ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም መካከል ፈለጉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 በመ​ን​ገ​ድም ከሰ​ዎች ጋር ያለ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ ያንድ ቀን መን​ገ​ድ​ንም ከሄዱ በኋላ ዕለ​ቱን ከዘ​መ​ዶቹ፥ ከሚ​ያ​ው​ቁ​ትም ዘንድ ፈለ​ጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 2:44
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤ በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ ልቤ በሐዘን ይሰበራል።


ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”


በዓሉ ከተፈጸመ በኋላ እነርሱ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀረ፤ ዮሴፍና ማርያም ግን እዚያ መቅረቱን አላወቁም ነበር።


ነገር ግን ሊያገኙት ስላልቻሉ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


ኢየሱስን በቅርብ ያውቁት የነበሩ ሰዎች ሁሉና ከገሊላ ጀምሮ ይከተሉት የነበሩ ሴቶችም በሩቅ ቆመው ይህን ነገር ይመለከቱ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች