Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 2:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ሕፃኑም እያደገና እየጠነከረ ሄደ፤ በጥበብም የተሞላ ሆነ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ ከእርሱ ጋር ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ሕፃኑም እያደገ፣ እየጠነከረም ሄደ፤ በጥበብ ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በርሱ ላይ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ሕፃኑም አደገ ጠነከረም፤ ጥበብም ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈ​ስም ጠነ​ከረ፤ ጥበ​ብ​ንም የተ​መላ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸጋ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 2:40
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት የተወደደ ሆኖ፥ በጥበብና በቁመት እያደገ ይሄድ ነበር።


ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤል ሕዝብ እስከ ታየበት ጊዜ ድረስ በበረሓ ኖረ።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በመካከላችን ኖረ፤ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ እንዳለው ያለውን ክብሩን አይተናል።


ወጣቱ ሳሙኤል ግን በቁመት እያደገ፥ በእግዚአብሔርና በሰውም ዘንድ ጸጋና ሞገስን እያገኘ ሄደ።


ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበር ሳሙኤል የሚናገረውን ቃል ሁሉ ይፈጽምለት ነበር፤


የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይገረሙ ነበር።


በደኅና እንድወለድ ያደረግኸኝ አንተ ነህ፤ የእናቴን ጡት በምጠባበት በሕፃንነቴ ወራት እንኳ የጠበቅኸኝ አንተ ነህ።


ሳሙኤል ግን ገና በልጅነቱ ከበፍታ የተሠራ ሸሚዝ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር፤ ይህም ቃል በዕብራይስጡ ካህኑ ለሚለብሰው ልብስ ወይም በደረቱ ላይ ስለሚያደርገው ነገር መጠሪያ ነው።


ሴቲቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሶምሶን ብላ ጠራችው፤ ልጁም አደገ፤ እግዚአብሔርም ባረከው፤


እንግዲህ ልጄ ሆይ! በኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጸጋ በርታ።


በቀረውስ በጌታና በእርሱም ታላቅ ኀይል በርቱ፤


ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስን ትንሣኤ በታላቅ ኀይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ ነበረ።


አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የተዋብክ ነህ፤ ንግግርህም ሞገስ የሞላበት ነው፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባርኮሃል።


እግዚአብሔርም ሐናን አስታወሳትና ሌሎች ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችን ወለደች፤ ወጣቱ ሳሙኤልም እግዚአብሔርን እያገለገለ አደገ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች