Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 19:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ ልብሳቸውንም በውርንጫው ጀርባ ላይ አንጥፈው ኢየሱስ እንዲቀመጥበት አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከዚያም ውርንጫውን ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሶቻቸውን በላዩ ጣል አድርገው ኢየሱስን በውርንጫው ላይ አስቀመጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ወደ ኢየሱስም አመጡት፤ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ወርውረው ኢየሱስን አስቀመጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ይዘ​ውም ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወሰ​ዱት፤ በው​ር​ን​ጫው ላይም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ጭነው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በዚያ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ወደ ኢየሱስም አመጡት፥ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ጭነው ኢየሱስን አስቀመጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 19:35
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።


ይህም የሆነው በነቢይ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፦


አህያዋንም ከነውርንጫዋ አመጡለት፤ ልብሳቸውንም በአህዮቹ ጀርባ ላይ አደረጉ፤ ኢየሱስም በዚያ ላይ ተቀመጠ።


እነርሱም “ለጌታ ስለሚያስፈልገው ነው” አሉ።


ኢየሱስ ሲሄድ ሳለ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገዱ ላይ ያነጥፉለት ነበር።


በማግስቱ ለፋሲካ በዓል የመጡ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የሚመጣ መሆኑን ሰሙ።


ኢየሱስ የአህያ ውርንጭላ አገኘና በእርሱ ላይ ተቀመጠ፤ ይህም የሆነው፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች