Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 17:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይተኛሉ፤ ከእነርሱም አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል እላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እላችኋለሁ፤ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ይተኛሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሁለተኛውም ይቀራል እላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሁለት ሰዎች በአ​ንድ አልጋ ይተ​ኛሉ፤ አን​ዱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይተ​ዋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እላችኋለሁ፥ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 17:34
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው።


“እንግዲህ ይህን ሁሉ ነገር አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፤


“በጠባብዋ በር ለመግባት ተጣጣሩ፤ በዚህች በር መግባት የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፤ ነገር ግን መግባት አይችሉም እላችኋለሁ።


ሁሉን ነገር አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁና እንግዲህ ተጠንቀቁ!


ታዲያ አንተ ለራስህ የተለየ መልካም ነገር እንዳደርግልህ ትፈልጋለህን? ይህን መፈለግ የለብህም፤ እኔ መቅሠፍትን በሰው ዘር ሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ ይሁን እንጂ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ ሌላው ቢቀር ሕይወትህ እንድትተርፍ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እነሆ፥ እኔ አስቀድሜ የተናገርኳቸው ነገሮች ሁሉ ተፈጽመዋል፤ አሁን ደግሞ ወደ ፊት ስለሚሆኑት አዳዲስ ነገሮች፥ ከመፈጸማቸው በፊት እናገራለሁ።”


የክፋትን ሥራ ከሚሠሩ ክፉ ሰዎች ጋር አትውሰደኝ፤ እነርሱ ከጐረቤቶቻቸው ጋር በሰላም ይነጋገራሉ፤ በልባቸው ግን ተንኰል አለ።


ደም አፍሳሾች ከሆኑ ኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን አትውሰድ፤ ሕይወቴንም አታጥፋ።


አይደለም! ንስሓ ባትገቡ እናንተም እንደእነርሱ ትጠፋላችሁ እላችኋለሁ።”


‘አይደለም፤ ንስሓ ባትገቡ እናንተም እንደእነርሱ ትጠፋላችሁ’ እላችኋለሁ።


በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ሌሎቹ ሁሉ እንኳ ቢክዱህ፥ እኔ ከቶ አልክድህም!” አለው።


ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ያድናታል።


ሁለት ሴቶች በአንድ ቦታ አብረው ይፈጫሉ፤ አንድዋ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ ትቀራለች። [


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች