Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 14:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይህን ብታደርግ እነርሱ ውለታ ለመክፈል ስለማይችሉ የተባረክህ ትሆናለህ። በጻድቃን ትንሣኤ ጊዜም እግዚአብሔር ይከፍልሃል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ትባረካለህም። እነዚህ ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ፣ በጻድቃንም ትንሣኤ ብድራትህ ይመለስልሃል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሚመልሱት አጸፋ የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አን​ተም ብፁዕ ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ከ​ፍ​ሉህ የላ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን ጻድ​ቃን በሚ​ነ​ሡ​በት ጊዜ ዋጋ​ህን ታገ​ኛ​ለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 14:14
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለድኾች የሚሰጥ ለእግዚአብሔር እንዳበደረ ይቈጠራል፤ እግዚአብሔርም የመልካም ሥራውን ዋጋ ይከፍለዋል።


እነርሱም ተስፋ እንደሚያደርጉት እኔም ጻድቃንና ኃጥአን ከሞት እንደሚነሡ በእግዚአብሔር ተስፋ አደርጋለሁ።


መልካም የሠሩ ከሞት ተነሥተው በሕይወት ይኖራሉ፤ ክፉ የሠሩ ግን ከሞት ተነሥተው ይፈረድባቸዋል።


እንግዲህ ምጽዋትህ በስውር ይሁን፤ በስውር የተሠራውን የሚያየው አባትህ፥ የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።


ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድኾችን፥ አካለ ስንኩሎችን፥ ሽባዎችን፥ ዕውሮችንም ሰዎች ጥራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች