Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 11:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 “እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኲራብ ውስጥ በክብር ወንበር ላይ መቀመጥ ትወዳላችሁ፤ እንዲሁም በአደባባይና በገበያ ቦታ ሰው ሁሉ እጅ እንዲነሣችሁ ትፈልጋላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 “እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፤ በምኵራብ የከበሬታ መቀመጫ፣ በገበያ ስፍራ የአክብሮት ሰላምታ ትወድዳላችሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኵራቦች የከበሬታን ወንበርንና በገበያ ቦታዎች ሰላምታን ትወዳላችሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እና​ንተ ግብ​ዞች ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! በም​ኵ​ራብ ፊት ለፊት መቀ​መ​ጥን፥ በገ​በ​ያም እጅ መነ​ሣ​ትን ትወ​ዳ​ላ​ች​ሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 እናንተ ፈሪሳውያን፥ በምኵራብ የከበሬታ ወንበር በገበያም ሰላምታ ስለምትወዱ፥ ወዮላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 11:43
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ረጃጅም ልብስ ለብሰው ወዲያና ወዲህ መዞርን፥ በገበያም የክብር ሰላምታ መቀበልን፥ በምኲራብ የክብር ወንበርን፥ በግብዣም የክብር ስፍራን ከሚወዱ ከሕግ መምህራን ተጠንቀቁ።


ከዚህ በፊት ለቤተ ክርስቲያን ደብዳቤ ጽፌአለሁ፤ ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን መሪ መሆን የሚፈልገው ዲዮትሬፊስ አሳቤን አልተቀበለም።


በትሕትና ተሞልታችሁ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ አድርጋችሁ ቊጠሩ እንጂ በራስ ወዳድነት ወይም “ያለ እኔ ማን አለ” በሚል ትምክሕት ምንም ነገር አታድርጉ።


እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ለመከባበርም ተሽቀዳደሙ፤


ትዕቢት ወደ ጥፋት ይወስዳል፤ ትምክሕተኛነትም ወደ ውድቀት ያደርሳል።


“ነገር ግን የዚህን ዘመን ሰዎች በምን አነጻጽራቸዋለሁ? በአደባባይ ተቀምጠው ጓደኞቻቸውን እየጠሩ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች