Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 11:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 እናንተ ሞኞች! የውጪውን የፈጠረ አምላክ የውስጡንስ አልፈጠረምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እናንተ ሞኞች፤ የውጭውን የፈጠረ የውስጡንም አልፈጠረምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 እናንተ ሞኞች! የውጭውን የፈጠረ እርሱ የውስጡንስ ደግሞ አለፈጠረምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እና​ንተ ሰነ​ፎች፥ የው​ጭ​ውን የፈ​ጠረ የው​ስ​ጡ​ንስ የፈ​ጠረ አይ​ደ​ለ​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 እናንት ደንቆሮዎች፥ የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አለፈጠረምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 11:40
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ግን ‘አንተ ሞኝ፥ ዛሬ በዚህች ሌሊት ነፍስህ ከአንተ ትወሰዳለች፤ ታዲያ ይህ ያከማቸኸው ሀብት ሁሉ ለማን ይሆናል?’ አለው።


አንተ ሞኝ! የምትዘራው እህል ካልሞተ ሕይወት አይኖረውም፤


አንተ ዕውር ፈሪሳዊ! አስቀድመህ ብርጭቆውንና ሳሕኑን ከውስጥ በኩል አጥራ! በዚያን ጊዜ በውጪም በኩል ንጹሕ ይሆናል።


ከዚህም በቀር እኛ ሁላችን የሚቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ፥ በሕይወት ለመኖር ለመንፈሳዊ አባታችን በይበልጥ መታዘዝ እንዴት አይገባንም!


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታስተውሉና ነቢያት የተናገሩትንም ሁሉ ከማመን ልባችሁ የዘገየ!


እናንተ ሞኞችና ዕውሮች! ከወርቁና ወርቁን ከሚቀድሰው ቤተ መቅደስ የቱ ይበልጣል?


ሰማይን የዘረጋ፥ ምድርን የመሠረተ፥ ለሰውም የሕይወትን እስትንፋስ የሰጠ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል እንዲህ ይላል፦


እናንተ ዐይን እያላችሁ የማታዩ፥ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ፥ እናንተ ሞኞችና ሰነፎች የሆናችሁ ሕዝብ ሆይ! ይህን ስሙ፤


እናንተ ዕውቀት የሌላችሁ፥ ዕውቀትን ለመገብየት ተማሩ፤ እናንተ ሞኞች፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጉ።


“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!


የሁላቸውንም ልብ የሠራ እርሱ ነው የሚያደርጉትን ሁሉ ይመለከታል።


ሞኞች በልባቸው፦ “እግዚአብሔር የለም” ይላሉ፤ እንደነዚህ ያሉት የተበላሹ ናቸው፤ አጸያፊ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፤ ከእነርሱ መካከል መልካም ነገርን የሚያደርግ አንድም የለም።


ሙሴና አሮን በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነህ፤ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?”


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ሰውን በመልካችንና በአምሳያችን እንፍጠር፤ ሰዎችም በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎች፥ በእንስሶችና በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች፥ እንዲሁም በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች