Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ድምፅዋንም ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፦ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ ከአንቺ የሚወለደውም የተባረከ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፤ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 በታ​ላቅ ቃልም ጮሃ እን​ዲህ አለች፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ፤ የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽም ፍሬ ቡሩክ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:42
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህ ይሉም ነበር፤ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው! ሰላም በሰማይ፥ ክብርም ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን!”


የቄናዊው የሔቤር ሚስት ያዔል፥ ከሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ትሁን፤ በድንኳን ከሚኖሩ ሴቶችም ሁሉ ይልቅ የተባረከች ትሁን፤


መልአኩም ወደ እርስዋ መጥቶ፦ “አንቺ ጸጋን የተሞላሽ፥ ሰላም ለአንቺ ይሁን! ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ [አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ]” አላት።


ትእዛዜን ስለ ፈጸምክ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።”


እግዚአብሔር እኔን ዝቅተኛ አገልጋይቱን ተመልክቶአልና፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ ይሉኛል፤


የዘለዓለም በረከትን ሰጠኸው፤ አንተም ከእርሱ ጋር በመገኘትህ ደስ ታሰኘዋለህ፤


የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።


እነርሱ በትውልዳቸው ከነገድ አባቶች የመጡ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የመጣው ከእነርሱ ዘር ነው፤ እርሱ ከሁሉ በላይ ነው፤ ለዘለዓለምም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን!


አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የተዋብክ ነህ፤ ንግግርህም ሞገስ የሞላበት ነው፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባርኮሃል።


ኤልሳቤጥ የማርያምን የሰላምታ ቃል በሰማች ጊዜ በማሕፀንዋ የነበረው ሕፃን ዘለለ። ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ፥


የጌታዬ እናት ልትጐበኘኝ መምጣትዋ ለእኔ እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች