Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እንዲሁም እኔ ከመጀመሪያው አንሥቼ ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ከመረመርኩ በኋላ ታሪኩን በቅደም ተከተል እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሆኖ አገኘሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ክቡር ቴዎፍሎስ ሆይ፤ እኔም በበኩሌ ሁሉን ከመሠረቱ በጥንቃቄ ከመረመርሁ በኋላ፣ ታሪኩን ቅደም ተከተሉን በጠበቀ ሁኔታ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከመጀመሪያው አንሥቶ ስለሆኑት ነገሮች ሁሉ በጥንቃቄ በመመርመር፥ ለአንተ ቅደም ተከተሉን የጠበቀ ታሪክ ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የከ​በ​ርህ ቴዎ​ፍ​ሎስ ሆይ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ተከ​ትዬ፥ ሁሉ​ንም በየ​ተ​ራው እው​ነ​ተ​ኛ​ውን እጽ​ፍ​ልህ ዘንድ መል​ካም ሁኖ ታየኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:3
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቴዎፍሎስ ሆይ! በመጀመሪያ መጽሐፌ ኢየሱስ የሠራውንና ያስተማረውን ሁሉ ጽፌአለሁ። የጻፍኩትም ኢየሱስ ሥራውን ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ


ጳውሎስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እጅግ የተከበርክ ፊስጦስ ሆይ! እውነተኛውንና ትክክለኛውን ነገር እናገራለሁ እንጂ አላበድኩም።


እጅግ የተከበርክ ፊልክስ ይህን መልካም አድራጎትህን በየቦታውና በየጊዜው የምንቀበለው ከፍ ባለ ምስጋና ነው።


“ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ፤ ለክቡር አገረ ገዢ ፊልክስ! ሰላም ለአንተ ይሁን!


ጴጥሮስ ግን እንዲህ ሲል ሁሉንም ነገር በተከታታይ ማስረዳት ጀመረ፦


“ስለዚህ የእኔ አሳብ ወደ እግዚአብሔር የሚመለሱትን አሕዛብ እንዳናስቸግራቸው ነው።


ወንድማችን አጵሎስ ከሌሎች ወንድሞች ጋር እናንተን እንዲጐበኛችሁ በጥብቅ ለምኜው ነበር፤ ነገር ግን እርሱ አሁን ወደ እናንተ ለመምጣት አልፈቀደም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።


በእኔ አስተያየት ግን ባል ሳታገባ ብቻዋን ብትሆን ይበልጥ ተደስታ ትኖራለች፤ እኔም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለኝ ይመስለኛል።


ይህን ስታደርግ ዝም በማለቴ እኔም እንደ አንተ የሆንኩ መሰለህን? አሁን ግን ፊት ለፊት ነገሩን ገልጬ እገሥጽሃለሁ።


ከእነዚህ ከሚከተሉት አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር ሌላ ከባድ ሸክም እንዳንጭንባችሁ መንፈስ ቅዱስና እኛ መልካም ሆኖ አግኝተነዋል፤


ስለዚህ በአንድነት ከተሰበሰብን በኋላ መልእክተኞችን መርጠን ከተወደዱት ወንድሞቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ልንልካቸው ተስማማን።


የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ በእኛ መካከል የተፈጸሙትን ነገሮች የሚገልጥ ታሪክ ከዚህ ቀደም ብዙዎች ጽፈዋል።


ጥበበኛው ጠቢብ ብቻ ሳይሆን ዕውቀትን ለሕዝቡ ማስተማር ቀጠለ፤ ብዙ ምሳሌዎችን መርምሮ ካጠና በኋላ በቅደም ተከተል አዘጋጀ፤


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤ አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤ እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል።


እውነት ምን እንደ ሆነም ያስተምሩሃል፤ “እውነትን ፈልገህ አቅርብ” ተብለህ ብትጠየቅም ትክክለኛውን መልስ ትሰጣለህ።


እዚያም ጥቂት ጊዜ ቈየ፤ ከዚህ በኋላ በገላትያና በፍርግያ ምድር ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ አማኞችን አበረታታ።


ይህን ትምህርት ለአማኞች ብታስገነዝብ የእምነትን ቃልና የምትከተለውን መልካም ትምህርት እየተመገብክ ያደግኽ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች