Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዘካርያስ ግን መልአኩን “ይህ ነገር እርግጥ መሆኑን በምን ዐውቃለሁ? እኔ አርጅቻለሁ፤ ሚስቴም በዕድሜዋ ገፍታለች” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዘካርያስም መልአኩን፣ “ይህን በምን ዐውቃለሁ? እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም በዕድሜ ገፍታለች” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዘካርያስም መልአኩን፦ “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም በዕድሜዋ ገፍታለችና ይህንን በምን አውቃለሁ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዘካ​ር​ያ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ እን​ዲህ አለው፥ “ይህ እን​ደ​ሚ​ሆን በምን አው​ቃ​ለሁ? እነሆ፥ እኔ አር​ጅ​ች​አ​ለሁ፤ የሚ​ስ​ቴም ዘመ​ንዋ አል​ፏል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ዘካርያስም መልአኩን፦ እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:18
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብራም ግን “ጌታ አምላክ ሆይ፥ ይህች ምድር የእኔ እንደምትሆን እንዴት ለማወቅ እችላለሁ?” ሲል ጠየቀ።


አብርሃም ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ ነገር ግን “ዕድሜው መቶ ዓመት የሆነው ሰው ልጅ መውለድ ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመትዋ ልጅ ልትወልድ ትችላለችን?” ብሎ በማሰብ ሳቀ፤


ስለዚህ ሣራ “እኔ አሁን እንዲህ ካረጀሁ በኋላ ጌታዬ አብርሃምም ካረጀ በኋላ እንዲህ ያለ ደስታ ሊኖረኝ ይችላልን?” ብላ በማሰብ ሳቀች።


በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።


ንጉሥ ሕዝቅያስም “ድኜ ወደ ቤተ መቅደስ ለመሄድ እንደምችል የማውቀው በምን ምልክት ነው?” ሲል ኢሳይያስን ጠየቀ።


ማርያም መልአኩን “እኔ ድንግል ነኝ፤ ታዲያ፥ ይህ ነገር እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለችው።


ኤልሳቤጥ መኻን ስለ ነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ ደግሞ ሁለቱም በጣም አርጅተው ነበር።


ዕድሜው መቶ ዓመት ያኽል ስለ ነበረ በሥጋው መድከም እንደ ሞተ በመሆን ምክንያት መውለድ እንደማይችልና ሣራም መኻንና ያረጀች በመሆንዋ መውለድ እንደማትችል ቢያውቅም በእምነቱ ደካማ አልሆነም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች