Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 7:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በእቶን የተጋገረው የእህል መባ ሁሉ፥ ወይም በመቀቀያ የበሰለውና በምጣድ የተጋገረው መሥዋዕት አድርጎ ላቀረበው ካህን ይሰጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ፣ በመቀቀያ ወይም በምጣድ የበሰለ ማንኛውም የእህል ቍርባን ለሚያቀርበው ካህን ይሰጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በምድጃ ላይ የተጋገረው፥ በመጥበሻም ወይም በምጣድ ላይ የተዘጋጀው የእህል ቁርባን ሁሉ ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረው የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ፥ በመ​ቀ​ቀ​ያም ወይም በም​ጣድ የበ​ሰ​ለው ሁሉ ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ካህን ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በእቶን የተጋገረው የእህል ቍርባን ሁሉ፥ በመቀቀያም ወይም በምጣድ የበሰለው ሁሉ ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 7:9
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ጊዜ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል በጋት ከተማ ላይ አደጋ ጥሎ ያዛት፤ ቀጥሎም በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ወሰነ።


የእህሉ መሥዋዕት፥ የኃጢአትና የበደል ስርየት መሥዋዕት ለእነርሱ ምግብ ይሁንላቸው፤ በእስራኤል ምድር ለእኔ ተለይቶ የተቀደሰውን ማናቸውንም መባ ሁሉ ይቀበሉ።


ቀሪው መባ ግን ለካህናቱ ይሰጥ፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ ተከፍሎ የተወሰደ በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።


ካህኑም በዚህ ዐይነት ስለዚያ ሰው ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትን ያቀርባል፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል፤ የቀረው ዱቄት የእህል መባ በሚቀርብበት ዐይነት ለካህኑ ይሁን።”


በዘይት የተለወሰም ቢሆን ወይም ደረቅ ያልበሰለው የእህል መባ ግን ትውልዳቸው ከአሮን ወገን ለሆነው ካህናት ሁሉ ይሰጥ፤ እርሱንም እኩል ይካፈሉት።


ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረበው እንስሳ፥ ቆዳው ተገፎ መሥዋዕቱን ላቀረበው ካህን ይሰጠዋል፤


ለእኔ ከሚቀርበው እጅግ ከተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ከእህል ቊርባን፥ ስለ ኃጢአት ስርየትና ስለ በደል ካሣ ከሚቀርበውም መባ ሁሉ፥ በእሳት የማይቃጠለው የመባ ድርሻ የአንተና የልጆችህ ነው።


በቤተ መቅደስ የሚያገለግሉ ምግባቸውን ከቤተ መቅደስ እንደሚያገኙና በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት የሚያቀርቡና የሚያገለግሉ ከመሥዋዕት ተካፍለው እንደሚበሉ ታውቁ የለምን?


ያለ ደመወዝ በራሱ ገንዘብ በወታደርነት የሚያገለግል ማነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላስ ማነው? መንጋ እየጠበቀ የመንጋውን ወተት የማይጠጣ ማን ነው?


ቃሉን የሚማር ሰው ከአስተማሪው ጋር መልካሙን ነገር ሁሉ ይካፈል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች