Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኢያሱና ሠራዊቱ ሁሉ የተሸነፉ በማስመሰል ወደ ኋላ በማፈግፈግ ወደ ምድረ በዳ ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኢያሱና እስራኤል በሙሉ ድል የተመቱ መስለው በመታየት፣ ወደ ምድረ በዳው ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ድል የተነሡ መስለው ከፊታቸው በምድረ በዳው መንገድ ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በደ​ረ​ሱ​ባ​ቸ​ውም ጊዜ ኢያ​ሱና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከፊ​ታ​ቸው አፈ​ገ​ፈጉ፤ በም​ድረ በዳው መን​ገ​ድም ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ድል የተነሡ መስለው ከፊታቸው በምድረ በዳው መንገድ ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:15
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሰሜን በኩል የሚገኘውም ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ወንዝ ተነሥቶ ወደ ኢያሪኮ ሰሜን ሽቅብ ይወጣና በምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው ኮረብታማ አገር በኩል እስከ ቤትአዌን በረሓ ይደርሳል፤


በዚህም ጊዜ ብንያማውያን መሸነፋቸውን ተገነዘቡ። ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን በጊብዓ አካባቢ አስፍረዋቸው በነበሩ የሽምቅ ወታደሮች በመተማመን ወደ ኋላ አፈግፍገው ስለ ነበረ ነው።


ለዮሴፍ ዘሮች የተመደበው የምድሪቱ ደቡባዊ ክፍል በኢያሪኮ አጠገብ ከዮርዳኖስ ወንዝ ይጀምራል፤ ይኸውም ከኢያሪኮ ምንጮች ምሥራቃዊ ጫፍ በመነሣት ወደ በረሓው ይዘልቃል፤ ከኢያሪኮም ተነሥቶ ወደ ኮረብታማው አገር በመውጣት እስከ ቤትኤል ይደርሳል።


ከእነዚህም ሁሉ ጋር በበረሓማው ምድር ቤትዐራባ፥ ሚዲን፥ ሴካካ፥


የዐይ ንጉሥ ይህን በአየ ጊዜ እርሱና የከተማው ሕዝብ እስራኤልን በጦርነት ለመግጠም ወደ ዓራባ ፊት ለፊት ወጡ። ከከተማው በስተጀርባ በኩል የደጀን ጦር መኖሩን አላወቁም ነበር።


ከእስራኤላውያንም ፊት አፈግፍገው ወደ በረሓው ሸሹ፤ ነገር ግን ማምለጥ አልቻሉም፤ በዋናው ሠራዊትና አሁን ከከተማው ውስጥ በመውጣት ላይ ባሉት ወታደሮች መካከል ተይዘው ተደመሰሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች