Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በማግስቱም ጠዋት ኢያሱ ቀደም ብሎ በመነሣት ሕዝቡን ጠራ፤ እርሱና የእስራኤል መሪዎች ሁሉ ዘማቹን ጦር ወደ ዐይ መምራት ጀመሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በማግስቱም ጧት ኢያሱ ማልዶ በመነሣት ወንዶቹን ሰበሰበ፤ እርሱና የእስራኤል አለቆችም ከፊት ሆነው እየመሯቸው ወደ ጋይ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኢያሱም ማልዶ በጠዋት ተነሣ፥ ሕዝቡንም ሰበሰበ፤ እርሱም ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ኢያ​ሱም ማልዶ ተነሣ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ቸው፤ እር​ሱም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከሕ​ዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ ሕዝቡንም አሰለፈ፥ እርሱም የእስራኤልም ሽማግሌዎች ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:10
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ።


ያለ ማመንታት ትእዛዞችህን ለመፈጸም እተጋለሁ።


በማግስቱ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፤ የሺጢምን ሰፈር ለቀው ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄዱ፤ ከመሻገራቸውም በፊት በዚያ ሰፈሩ፤


በማግስቱ ኢያሱ በማለዳ ተነሣ፤ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸከሙ።


በማግስቱም ማለዳ ኢያሱ እስራኤላውያንን በየነገዳቸው አምጥቶ አቀረባቸው፤ ከዚያም የይሁዳ ነገድ ለብቻው ተለየ፤


ከእርሱም ጋር የነበረው ሠራዊት ወደ ፊት ቀድሞ በመጓዝ ወደ ከተማይቱ ቀረበ፤ በስተሰሜንም በኩል በእርሱና በዐይ መካከል ካለው ሸለቆ ማዶ ሰፈረ።


ከዚህ በኋላ ኢያሱ ወታደሮቹን ላከ፤ ከዐይ በስተምዕራብ በኩል በዐይና በቤትኤል መካከል ድብቅ ጦር ሆነው ቈዩ፤ ኢያሱም በሠራዊቱ መካከል ዐደረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች