Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 24:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እናንተ በማረስ ያልደከማችሁበትን የለማ ምድርና ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች መኖሪያ አድርጌ ሰጠኋችሁ፤ እነሆ፥ አሁን ያልተከላችሁትን የወይን ተክልና ያልደከማችሁበትን የወይራ ዛፍ ፍሬ እየተመገባችሁ ትኖራላችሁ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ ያልደከማችሁበትን ምድርና ያልሠራችኋቸውን ከተሞች ሰጠኋችሁ። እነሆ፣ በከተሞቹ ትኖራላችሁ፤ ካልተከላችሁት የወይን ተክልና የወይራ ዛፍ ትበላላችሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች ሰጠኋችሁ፥ ተቀመጣችሁባቸውም፤ ካልተከላችኋቸውም ከወይንና ከወይራ በላችሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ት​ንም ምድር፥ ያል​ሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውም፤ ካል​ተ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከወ​ይ​ንና ከወ​ይራ በላ​ችሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች ሰጠኋችሁ፥ ተቀመጣችሁባቸውም፥ ካልተከላችኋቸውም ከወይንና ከወይራ በላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 24:13
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ አወርሳቸው ዘንድ በመሐላ ቃል ኪዳን ወደገባሁባት ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስትም አድርጌ አወርሳችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”


ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ የሚተላለፍ ሀብት ያገኛል፤ የኃጢአተኞችን ሀብት ግን ቅን ሰዎች ይወርሱታል።


“እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚኖሩትን ሕዝቦች ደምስሶ ከተሞቻቸውንና ቤቶቻቸውንም ወርሰህ በዚያ መኖር በምትጀምሩበት ጊዜ፥


እነሆ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካሚቱ ለምለም ምድር ሊያስገባህ አምጥቶሃል፤ ያቺም ምድር ከሸለቆዎችና ከኮረብቶች የሚመነጩ ወንዞችና ጅረቶች፥ ፈሳሾች ምንጮችም ይገኙበታል፤


ይሁን እንጂ ኢያሱ ካቃጠላት ከሐጾር በቀር እስራኤላውያን በኮረብታ ላይ የተሠሩ ከተሞችን አላቃጠሉም።


በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት የገባው ቃል ኪዳን ሁሉ ተፈጸመ እንጂ አንድም የቀረ የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች