Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 23:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በመካከላችሁ ከቀሩት ሕዝቦች ጋር ከቶ አትተባበሩ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፤ በእነርሱም አትማሉ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች አትሁኑ፤ አትስገዱላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ ሕዝቦች ጋራ አትተባበሩ፤ የአማልክታቸውን ስም አትጥሩ፤ አትማሉባቸው፤ አታገልግሏቸው፤ አትስገዱላቸውም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ከእነዚህ አሕዛብ ጋር አትቀላቀሉ፤ የአማልክቶቻቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ አት​ግቡ፤ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስሞች በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ጠሩ፤ አት​ማ​ሉ​ባ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኳ​ቸ​ውም፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፥ የአማልክቶቻቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 23:7
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እኔ እግዚአብሔር የነገርኳችሁን ሁሉ በጥንቃቄ አድምጡ፤ ወደ ሌሎች አማልክት አትጸልዩ፤ ሌላው ቀርቶ ስማቸውን እንኳ አትጥሩ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን ትተው ሐሰተኞች አማልክትን ያመልካሉ፤ ታዲያ እኔ የእነርሱን ኃጢአት ይቅር የምለው ለምንድን ነው? እኔ ለሕዝቤ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ሁሉ በመስጠት እንዲጠግቡ አደረግሁ፤ እነርሱ ግን አመንዝሮች ሆኑ፤ ማደሪያቸውም በአመንዝሮች ቤት ሆነ።


ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩ ብዙ ሐዘን ይደርስባቸዋል፤ እኔ እንደነዚህ ላሉት አማልክት የደም መሥዋዕትን አላቀርብም፤ እነርሱንም አላመልክም።


እነዚያ ሕዝቦች በአገርህ እንዲኖሩ አትፍቀድላቸው፤ የምትፈቅድላቸው ከሆነ ግን ኃጢአት በመሥራት እኔን እንድትበድል ያደርጉሃል፤ ለአማልክቶቻቸውም ብትሰግድ ለሞት የሚያደርስ ወጥመድ ይሆንብሃል።”


ወደ ብርሃን አውጥታችሁ አጋልጡት እንጂ ፍሬቢስ ከሆነ ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ።


አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”


ጣራ ላይ ወጥተው ለፀሐይ፥ ለጨረቃና ለከዋክብት የሚሰግዱትን አጠፋለሁ፤ እኔን እያመለኩና በስሜ እየማሉ፥ ዘወር ብለው ደግሞ ሚልኮም ተብሎ በሚጠራው ጣዖት ስም የሚምሉትን እደመስሳለሁ።


ክፉ ሰዎች በሚሄዱበት መንገድ አትሂድ፤ ምሳሌነታቸውንም አትከተል።


እናንተ ግን ከእግዚአብሔር ርቃችሁ በእናንተ መካከል ከቀሩት ከእነዚህ ሕዝቦች ጋር ብትተባበሩ፥ እናንተ የእነርሱን ሴቶች እነርሱ ደግሞ የእናንተን ሴቶች በመጋባት ብትተሳሰሩ፥


ከአንደበትዋ የ“በዓል” ጣዖቶችን ስም ለማስወግድ የእነርሱ ስም ዳግመኛ አይጠራም።


የነቦን፥ በኋላ ስሙ የተለወጠው የባዓልመዖንንና የሲብማን ከተሞች አደሰ፤ እነርሱም ላደሱአቸው ከተሞች ሁሉ አዲስ ስም አወጡላቸው።


እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።


አምላክህን እግዚአብሔርን በመፍራት አክብረው፤ እርሱን ብቻ አምልክ፤ መሐላህም በእርሱ ስም ብቻ ይሁን።


አምላክህን እግዚአብሔርን በመፍራት ለእርሱ ታዘዝ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ፤ ለእርሱ ታማኝ ሆነህ በእርሱ ስም ብቻ ማል።


ይልቅስ እስከ አሁን እንዳደረጋችሁት ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሁኑ፤


የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤


በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ አሳዳችሁ ካላጠፋችሁ ግን ያስቀራችኋቸው ለዐይናችሁ እንደ ስንጥር ለጐናችሁም እንደ እሾኽ በመሆን ያስቸግሩአችኋል፤ በምትቀመጡባትም ምድር ዘወትር ጦርነት በማስነሣት ያስጨንቁአችኋል።


በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ የሚሰግዱላቸውን ሌሎችን ባዕዳን አማልክት አታምልኩ፤


ስለዚህም የሀገሬን ንጉሥ በማጀብ ሪሞን የተባለ የሶርያ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም ይቅር ይለኛል።”


እግዚአብሔር ለጣዖት እንዳይሰግዱ ያዘዛቸውንም ሕግ ሁሉ አፈረሱ።


ነገር ግን አንተና ሕዝብህ እኔ የሰጠኋችሁን ሕጎችና ትእዛዞች ባትጠብቁ፥ ባዕዳን አማልክትንም ብታመልኩና፥ ብትሰግዱላቸው፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች