Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 22:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ስለዚህም የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሐስ እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን ዐወቅን፤ እናንተ በእርሱ ላይ አላመፃችሁም፤ ስለዚህም የእስራኤልን ሕዝብ ከእግዚአብሔር ቅጣት አድናችኋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም፣ የሮቤልን የጋድንና የምናሴን ወገኖች “በዚህ ነገር እግዚአብሔርን አልበደላችሁምና፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ መሆኑን ዛሬ ዐውቀናል፤ እነሆ እስራኤላውያንን ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “ይህን መተላለፍ በጌታ ላይ አላደረጋችሁምና ጌታ በመካከላችን እንዳለ ዛሬ አውቀናል፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከጌታ እጅ አድናችኋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ “ይህን መተ​ላ​ለፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን እን​ዳለ ዛሬ እና​ው​ቃ​ለን፤ አሁን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አድ​ና​ች​ኋል” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች፦ ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፥ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 22:31
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤


በልቡ የተሰወረው ነገር ይገለጣል፤ በግንባሩም ተደፍቶ “በእርግጥ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነው!” በማለት ለእግዚአብሔር ይሰግዳል።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።


በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”


በእናንተ መካከል ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ስለ ሆነ በጽዮን የምትኖሩ ሁሉ ‘እልል’ በሉ!”


“እግዚአብሔር በብዙ ሺህ ከሚቈጠሩት ታላላቅ ሠረገላዎች ጋር ከሲና ወደ ተቀደሰው መቅደሱ ይመጣል።


ኢያሱም ንግግሩን በመቀጠል፦ “ሕያው እግዚአብሔር በመካከላችሁ መሆኑን የምታውቁት እናንተ ወደ ፊት እየገፋችሁ በሄዳችሁ መጠን እርሱ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ሒዋውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ የሚያስወጣ በመሆኑ ነው።


በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ሕዝቡ ቤተ መቅደስ ይሥሩልኝ፤


ካህኑ ፊንሐስና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝቡ የላካቸው የምዕራብ ነገዶች የቤተሰብ አለቆች የሆኑት ታላላቅ ሰዎች፥ የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ በሚኖሩ የምናሴ ነገዶች ሕዝብ የተናገሩትን ሰምተው መልሱ አረካቸው፤


ከዚህም በኋላ የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና መሪዎቹ በገለዓድ ከሚገኙት ከሮቤልና ከጋድ ሕዝቦች ዘንድ በከነዓን ምድር ወደሚገኙት ወደ እስራኤል ሕዝብ ተመልሰው በመምጣት፥ ያገኙትን ማስረጃ አቀረቡ፤


ቡቂ የአቢሹዓ ልጅ፥ አቢሹዓ የፊንሐስ ልጅ፥ ፊንሐስ የአልዓዛር ልጅ፥ አልዓዛር የሊቀ ካህናቱ የአሮን ልጅ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች