Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 21:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከመራሪ የተወለዱትም ቀሪዎቹ ሌዋውያን ከዛብሎን ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተረከቡአቸው አራት ከተሞች ዮቅነዓም፥ ቃርታ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ከዛብሎን ነገድ፣ ዮቅንዓም፣ ቀርታ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንና መሰማሪያዋን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ከሌ​ዋ​ው​ያን ለቀ​ሩት ለሜ​ራሪ ልጆች ወገን ከዛ​ብ​ሎን ነገድ ዮቅ​ና​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰምርያዋን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 21:34
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለቀሪዎቹ የመራሪ ጐሣ ቤተሰቦች የሚከተሉት ከተሞች በዙሪያቸው ከሚገኙት የግጦሽ ቦታዎች ጋር ተመድበውላቸው ነበር፦ በዛብሎን ግዛት ሪሞኖና ታቦር፤


ለመራሪ ጐሣ እንደየወገናቸው ከሮቤል፥ ከጋድና ከዛብሎን ይዞታዎች ተከፍለው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተመደቡላቸው።


እርሱም ቃጣት፥ ናህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላና ቤተልሔም ተብለው የሚጠሩትን ዐሥራ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያጠቃልላል፤


ድንበሩም ከዚያ በመነሣት ከዳባሼትና በዮቅነዓም ምዕራብ ከሚገኘው ወንዝ እየተዋሰነ በምሥራቅ በኩል እስከ ማርዕላ ይደርሳል።


ቄዴሽ፥ በቀርሜሎስ የሚገኘው ዮቅነዓም፥


የጌርሾን ጐሣ በሙሉ በድምሩ ዐሥራ ሦስት ከተሞችን ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ተረከቡ።


ዲምናና ናህላል ናቸው።


እንዲሁም ለመራሪ ጐሣ በየወገናቸው ከሮቤል፥ ከጋድና ከዛብሎን ግዛቶች በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተመድበው ነበር።


ሌዋውያን የሆኑ የእነርሱ ወገኖችም በእግዚአብሔር ቤት ሌላውን ተግባር ሁሉ ያከናውኑ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች