Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 21:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከብንያም ግዛት ተከፍለው አራት ከተሞች ተሰጡአቸው። እነርሱም ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ገባዖን፥ ጌባዕ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከብንያም ነገድ፣ ገባዖን፣ ጌባዕ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማሪያዋን፥ ናሲብንና መሰማሪያዋን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ገባ​ዖ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጋቲ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰምርያዋን፥ ናሲብንና መሰምርያዋን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 21:17
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህም በኋላ ንጉሥ አሳ፥ ባዕሻ ራማን ለመመሸግ አከማችቶት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ከዚያ ለማንሣት እንዲረዳው ሕዝቡ አንድም ሳይቀር እንዲመጣ ወደ ይሁዳ ግዛቶች ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ንጉሥ አሳ ከዚያ የተገኘውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ ወስዶ ምጽጳንና በብንያም ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የጌባዕን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራበት።


በይሁዳ ከተሞችና በመላ ሀገሪቱ ከገባዕ እስከ ቤርሳቤህ የነበሩትን ካህናት ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣ፤ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ርኩስ መሆናቸውን ዐወጀ፤ እንዲሁም የከተማይቱ ገዢ ኢያሱ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ከዋናው ቅጽር በር በስተ ግራ በኩል ባሠራው ቅጽር በር አጠገብ የሚገኙትን መስገጃዎች አፈራረሰ።


በብንያም ግዛትም ጌባዕ፥ ዓሌሜትና ዐናቶት ተብለው የሚጠሩት ከተሞች ከነግጦሽ ቦታዎቻቸው ለአሮን ልጆች የተሰጡ ነበሩ፤ እንግዲህ ለአሮን ዘሮች ቤተሰብ ሁሉ መኖሪያ የሚሆኑ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ነበሩ።


የኤሁድ ዘሮች ናዕማን፥ አሒያና ጌራ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጌባዕ ይኖሩ ለነበሩት በኋላ ግን ከዚያ ተባረው ወደ ማናሐት ሄደው በዚያ ለኖሩ ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ ወደዚያም የመራቸው የዑዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበር።


ከቤትጊልጋል፥ ከጌባዕና ከዓዝማዌት ተሰብስበው መጡ፤


መተላለፊያውን አልፈው ዐዳር በጌባዕ ሆነ በራማ ከተማ የሚኖሩ ሁሉ ደነገጡ፤ በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ የሚኖሩትም ሁሉ ሸሹ።


በሰሜን ከጌባዕ አንሥቶ ኢየሩሳሌምን በደቡብ በኩል አልፎ እስከ ሪሞን ድረስ ያለው አውራጃ ደልዳላ ይሆናል፤ ኢየሩሳሌም በዙሪያዋ ካለው ምድር በላይ ከፍ ትላለች፤ ከተማይቱም ከብንያም በር አንሥቶ በቀድሞው በር አቅጣጫ እስከ ማእዘን በር እንዲሁም ከሐናንኤል ግንብ አንሥቶ እስከ ቤተ መንግሥቱ ወይን መጭመቂያው ድረስ ከፍ በማለት ጸንታ ትኖራለች።


ዐናቶትና ዐልሞን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።


የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በዐይ ከተማዎች ላይ ያደረገውን ሁሉ ስለ ሰሙ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች