Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 2:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሰዎቹም እንዲህ አሉአት፤ “እኛ በገባንልሽ ቃል መሠረት ባንፈጽም እግዚአብሔር በሞት ይቅጣን! እኛ ያደረግነውን ሁሉ ለማንም ባትነግሪ፥ እግዚአብሔር ይህቺን ምድር ለእኛ አሳልፎ በሚሰጠን ጊዜ ለአንቺ መልካም ነገር ለማድረግ ቃል እንገባለን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሰዎቹም፣ “የእናንተን ሞት ለእኛ ያድርገው! እኛ የምናደርገውን ሁሉ ካልተናገራችሁ፣ እግዚአብሔር ምድሪቱን በሚሰጠን ጊዜ፣ በጎነትና ታማኝነት እናሳይሻለን” አሏት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሰዎቹም እንዲህ አሉአት፦ “ይህን ነገራችንን ለማንም ባትናገሩ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ ለሞት ይሆናል፤ ጌታም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ለአንቺ ቸርነትንና ታማኝነትን እናደርጋለን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሰዎ​ቹም፥ “ሕይ​ወ​ታ​ች​ንን ስለ እና​ንተ አሳ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን” አሉ፤ እር​ስ​ዋም አለች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ጣ​ችሁ ጊዜ ቸር​ነ​ት​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ር​ጉ​ል​ና​ላ​ችሁ።” ሰዎ​ቹም፥ “ይህን ነገ​ራ​ች​ንን ባት​ገ​ልጪ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ራ​ች​ሁን በእ​ው​ነት አሳ​ልፎ ከሰ​ጠን ከአ​ንቺ ጋር ቸር​ነ​ትን እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሏት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሰዎቹም፦ ይህን ነገራችንን ባትገልጪ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ ለሞት ይሆናል፥ እግዚአብሔርም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ከአንቺ ጋር ቸርነትንና እውነትን እናደርጋለን አሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 2:14
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምሕረትን ስለሚያገኙ ምሕረትን የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።


ወዳጆች ሳይሆኑ ወዳጆች መስለው የሚታዩ አሉ፤ እውነተኛ ወዳጅ ግን ከወንድም ይበልጣል።


እንግዲህ የጌታዬን ዐደራ በእውነት ተቀብላችሁ እርሱን ደስ ለማሰኘት የምትፈቅዱ እንደ ሆነ ንገሩኝ፤ የማትፈቅዱም እንደ ሆነ ቊርጡን ንገሩኝ፤ እኔም እግዚአብሔር ወደሚመራኝ እሄዳለሁ።”


ንጉሡም በአጠገቡ ሲያልፍ፥ ነቢዩ ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ! እኔ በጦርነት ውስጥ በውጊያ ላይ ነበርኩ፤ በዚያን ጊዜም ከወታደሮቹ አንዱ ከጠላት ወገን አንድን ሰው ማርኮ በማምጣት ‘ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢያመልጥ ግን በእርሱ ፈንታ አንተ ትገደላለህ ወይም ሠላሳ አራት ኪሎ የሚመዝን ጥሬ ብር መቀጫ ትከፍላለህ’ አለኝ።


አንድ ቀን ዳዊት “ስለ ዮናታን ስል ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤተሰብ ከሞት የተረፈ ሰው አለን?” ብሎ ጠየቀ።


በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለ ተማመንን የሰጠኸኝን የተቀደሰ ተስፋ በመጠበቅ እባክህ ለእኔ ለአገልጋይህ መልካም ነገር አድርግልኝ፤ ወንጀለኛ ሆኜ ከተገኘሁ ግን አንተው ራስህ ግደለኝ እንጂ እንዲገድለኝ ወደ አባትህ ለምን ትወስደኛለህ?”


ነገር ግን ጋለሞታይቱ ረዓብ ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ የላካቸውን ሁለቱን ሰላዮች ደብቃ ከሞት ስላዳነች እርሱ እርስዋን፥ ቤተ ዘመዶችዋንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሌሎች ሰዎች ሁሉ ከሞት አተረፈ፤ የእርስዋም ዘሮች እስከ አሁን ድረስ በእስራኤል ምድር ይኖራሉ።


“በከተማይቱና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር የተረገመ ሆኖ መደምሰስ አለበት፤ ሴትኛ ዐዳሪዋ ግን የላክናቸውን ሰላዮች ደብቃ ስላዳነች መትረፍ የሚገባቸው እርስዋና ከእርስዋ ጋር በቤትዋ ያሉት ብቻ ናቸው።


አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼን፥ እኅቶቼንና የእነርሱን ቤተሰቦች ሁሉ ከሞት ለማዳን ቃል ግቡልኝ!”


ረዓብ የምትኖርበት ቤት ከከተማይቱ ቅጽር ግንብ ተጠግቶ በውስጥ በኩል የተሠራ ስለ ነበር ሰዎቹ በመስኮት በኩል ቊልቊል በተለቀቀ ገመድ ተንጠልጥለው ወደ ታች እንዲወርዱ አደረገች፤


ያዕቆብ የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ፥ በምሞትበት ጊዜ በግብጽ ምድር እንዳትቀብረኝ፥ እጅህን በጒልበቴ ላይ አኑረህ በመሐላ ቃል ግባልኝ።


ኢያሱ ሰላዮች ሆነው የተላኩትን ሁለት ሰዎች “ወደ ጋለሞታይቱ ረዓብ ቤት ሄዳችሁ በገባችሁላት የተስፋ ቃል መሠረት እርስዋንና ቤተሰብዋን አውጡ” አላቸው።


ዳዊት ወደ ያቤሽ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፦ “እርሱን በመቅበር ለጌታችሁ ለሳኦል ቸርነትን ስላሳያችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።


ደግሞም እግዚአብሔር ቸርነቱንና ታማኝነቱን ይግለጥላችሁ፤ እናንተ ስለ ፈጸማችሁት መልካም ነገር እኔም ለእናንተ ወሮታችሁን እመልሳለሁ።


ክፉ የሚያቅዱ ሰዎች ስሕተተኞች አይደሉምን? መልካምን ነገር የሚያቅዱ ግን ምሕረትንና ታማኝነትን ያገኛሉ።


አዛዡም “ይህን ነገር ለእኔ መንገርህን ለማንም አትግለጥ” ብሎ ልጁን አሰናበተው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች