Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 19:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ወደ ዔብሮን፥ ረሖብ፥ ሐሞንና ቃና አልፎ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በመቀጠልም ወደ ዔብሮን፣ ወደ ረአብ፣ እንዲሁም ወደ ሐሞንና ወደ ቃና ሽቅብ ወጥቶ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከዚ​ያም ወደ ኤብ​ሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜ​ማ​ህን፥ ወደ ቀን​ታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደ​ር​ሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 19:28
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአሴር ነገድ በዓኮ፥ በሲዶና፥ በአሕላብ፥ በአክዚብ፥ በሔልባ፥ በአፌቅና በረሖብ ይኖሩ የነበሩትን ኗሪዎች አላባረሩም ነበር።


እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በእነርሱ ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረጋቸው፤ እስራኤላውያንም መተው በሰሜን እስከ ሚስረፎትማይምና እስከ ታላቂቱ ሲዶና፥ በምሥራቅም እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ ሳይተርፍ ሁሉንም ፈጁአቸው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ውሃውን የወይን ጠጅ ወደ ለወጠባት በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ እንደገና ተመለሰ፤ በዚያን ጊዜ በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት አንድ የቤተ መንግሥት ሹም ነበረ።


ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።


በሦስተኛው ቀን፥ በገሊላ ምድር በምትገኘው ቃና በምትባል ከተማ ሠርግ ነበረ፤ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች።


“አንቺ የሲዶን ከተማ ሆይ! የደስታሽ ዘመን አክትሞአል፤ ሕዝብሽ ተጨቊነዋል፤ ወደ ቆጵሮስ ሸሽተው ቢያመልጡ እንኳ እዚያ በሰላም አይኖሩም” ብሎአል።


የሲዶና ከተማ ሆይ! አንቺ በባሕር አጠገብ የተገነባሽ ጠንካራ ምሽግ ነሽ፤ ነገር ግን አንቺ ባል አግብታ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወልዳ እንዳላሳደገች ሴት የተዋረድሽ ትሆኚአለሽ።


መርከበኞች ያበለጸጉአችሁ እናንተ የደሴቲቱ ሕዝብና የሲዶን ነጋዴዎች በሐዘን ጸጥ በሉ!


በዚህ ዐይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ በስተደቡብ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ በስተ ምሥራቅ እስከ ሰዶም፥ ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ሆነ።


በማግስቱ ወደ ሲዶና ደረስን፤ ዩልዮስ ለጳውሎስ ደግ ስለ ነበረ ወደ ወዳጆቹ ሄዶ የሚያስፈልገውን ርዳታ እንዲያደርጉለት ፈቀደለት።


ቀጥለውም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ምዕራብ ታጥፈው ወደ ሲዶና ሄዱ፤


ሔልቃትና ረሖብ ናቸው፤


የላይሽ ሕዝብ ከማንም ጋር ግንኙነት ስላልነበራቸውና ከሲዶንም ርቀው ይኖሩ ስለ ነበረ የሚያድናቸው አልተገኘም። ከተማዋ በቤትረሖብ አጠገብ በሚገኝ ሸለቆ ውስጥ ነበረች፤ የዳን ሰዎችም ከተማዋን እንደገና ሠርተው ኖሩባት።


ቀጥሎም በደቡብ በኩል ወደተመሸገችው ወደ ጢሮስ ከተማና እንዲሁም ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ሁሉ ሄዱ፤ በመጨረሻም በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ዘለቁ፤


“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ሲዶና መልሰህ በእርስዋ ላይ ትንቢት ተናገር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች