ኢያሱ 18:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ሰዎቹም በአገሪቱ በመላ ተዘዋወሩ፤ ከተሞቹንም ሁሉ መዝግበው ምድሪቱ ለሰባት ነገድ እንዴት እንደምትከፈል በጽሑፍ ገለጡ፤ ከዚህም በኋላ ኢያሱ ወዳለበት ወደ ሴሎ ተመልሰው መጡ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ስለዚህም ሰዎቹ ሄደው ምድሪቱን ተዘዋውረው አዩ፤ ከነ ከተሞቿም ሰባት ቦታ ከፍለው በጥቅልል ብራና ላይ በዝርዝር ጻፉ፤ ከዚያም በሴሎ ሰፈር ወዳለው ወደ ኢያሱ ተመለሱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ዞሩ፥ በከተሞቹም ልክ በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ በመጽሐፍም ጻፉት፤ ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ዞሩ፥ አዩትም፤ እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፤ በመጽሐፍም ጻፉት፤ ወደ ኢያሱም አመጡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ዞሩ፥ እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ በመጽሐፍም ጻፉት፥ ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ። ምዕራፉን ተመልከት |