Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 16:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የኤፍሬም ነገድ የርስት ድርሻ በየወገናቸው ይህ ነው፤ ድንበራቸው ከዐጣሮትአዳር በምሥራቅ በኩል ወደ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለኤፍሬም ወገን በየጐሣ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፤ ድንበሩ በምሥራቅ በኩል ከአጣሮት አዳር ተነሥቶ እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣና፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፤ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮትአዳር እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ድረስ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የኤ​ፍ​ሬ​ምም ልጆች ድን​በር በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ደ​ዚህ ነበረ፤ የር​ስ​ታ​ቸው ድን​በር ከአ​ጣ​ሮ​ትና፥ ከኤ​ሮሕ ምሥ​ራቅ ከጋ​ዛራ እስከ ላይ​ኛው ቤቶ​ሮን ድረስ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፥ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮትአዳር እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ድረስ ነበረ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 16:5
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይኸው ድንበር በደቡብ በኩል ቀድሞ ሎዛ ተብላ ትጠራ ወደነበረችው ወደ ቤትኤል ይወጣና በታችኛው ቤትሖሮን ተራራ በኩል ወደ ዐጣሮትአዳር ይወርዳል።


ከቤትኤልም ተነሥቶ አርካውያን የሚኖሩበትን ዐጣሮትአዳርን በማለፍ ወደ ሎዛ ይዘልቃል።


እግዚአብሔርም በእስራኤል ሠራዊት ፊት አሞራውያን በድንጋጤ እንዲሸበሩ አደረገ፤ እስራኤላውያንም እነርሱን በገባዖን ዐረዱአቸው፤ የቀሩትንም በቤትሖሮን በኩል እስከ ተራራው መተላለፊያ ቊልቊለት እስከ ዐዜቃና እስከ ማቄዳ ድረስ አሳደዱአቸው።


ኤፍሬም፥ ሼኢራ ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ እርስዋም የላይኛውንና የታችኛውን ቤትሖሮን፥ እንዲሁም ዑዜንሼኢራ ተብለው የሚጠሩትን ከተማዎች አሠራች።


ኤፍሬም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከምናሴ ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤


በዚያም አበኔር ኢያቡስቴን በገለዓድ ግዛቶች፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም ይኸውም በመላው እስራኤል ላይ እንዲነግሥ አደረገ።


የኤፍሬም ዘሮች በሙሉ ወስደው የራሳቸው መኖሪያ ያደረጉት ግዛት ቤትኤልና በዙሪያዋ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞችን ሲሆን፥ በምሥራቅ በኩል እስከ ናዕራን፥ በምዕራብ እስከ ጌዜር፥ እንዲሁም በጌዜር ዙሪያ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞችን ያጠቃልል ነበር፤ እንዲሁም ሴኬምንና ዓያን በዙሪያቸው የሚገኙትንም ታናናሽ ከተሞች ይጨምራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች