Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 11:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዐናቅ ዘሮች በእስራኤል ምድር የተረፈ አልነበረም፤ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ በጋዛ፥ በጋትና በአሽዶድ ይኖሩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፣ በጋትና በአሽዶድ ሲቀሩ፣ በእስራኤል የቀሩ የዔናቅ ዘሮች ግን አልነበሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በጋዛ፥ በጌ​ትም፥ በአ​ዛ​ጦ​ንም ከቀ​ሩት በቀር በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ከኤ​ና​ቃ​ው​ያን ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 11:22
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከጋት ከተማ የመጣ፥ ጎልያድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ግዙፍ ሰው፥ ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጥቶ እስራኤላውያንን መፈታተን ጀመረ፤ የዚያም ሰው ቁመት ሦስት ሜትር ያኽል ነበር፤


በአሽዶድም አቅራቢያ ከዔቅሮን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር የተሠሩ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት በሆነው በሣርጎን ትእዛዝ የአሦራውያን ጦር አዛዥ የፍልስጥኤማውያን ከተማ በሆነችው በአሽዶድ ላይ አደጋ ጣለ፤


ዖዝያ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ የጋትን፥ የያብኔንና የአሽዶድን ከተማዎች ቅጽሮችን አፈራረሰ፤ በአሽዶድ አጠገብና በቀሩትም የፍልስጥኤም ግዛት ውስጥ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ።


ጥቂት ዘግየት ብሎም ንጉሥ ዳዊት እንደገና በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ በመጣል ድል አደረጋቸው፤ አስገበራቸውም፤ የጋትን ከተማና በዙሪያዋ ያሉትን መንደሮች ከእነርሱ ቊጥጥር ነጻ አደረገ፤


በሪዓና ሴማዕ በአያሎን ከተማ ለሰፈሩት ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም በጋት ከተማ የሚኖረውን ሕዝብ አባረሩ፤


ከሦስት ዓመት በኋላ ግን ሁለቱ የሺምዒ አገልጋዮች የማዕካ ልጅ ወደ ሆነው አኪሽ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጋት ንጉሥ ኰብልለው ሄዱ፤ ሺምዒም ባሪያዎቹ በጋት መኖራቸው ተነገረው፤


ፍልስጥኤማውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከማረኩ በኋላ ከአቤንዔዜር አሽዶድ ተብላ ወደምትጠራ ከተማቸው ወሰዱአት።


በምድሪቱ ላይ የቀሩትም፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መሪዎች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከባዓልሔርሞን ተራራ አንሥቶ እስከ ሐማት ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች የሚኖሩት ሒዋውያን ነበሩ።


ፊልጶስ ግን በአዞጦስ ተገኘ፤ ወደ ቂሳርያም እስከ መጣ ድረስ በየከተሞቹ ሁሉ እየሄደ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።


በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ግዙፋን የሆኑ ቁመተ ረጃጅሞችና ብርቱዎች ናቸው፤ እነርሱም ‘ማንም ሊቋቋማቸው የማይችል የዔናቅ ዘሮች ናቸው’ ሲባል ሰምተሃል፤


ካሌብም የዐናቅን ሦስት ልጆች ሼሻይን፥ አሒማንና ታልማይን አባረረ፤ እነርሱም የዐናቅ ዘሮች ነበሩ።


የይሁዳም ነገድ ጋዛንና አስቀሎናን፥ አቃሮንንና አካባቢዎቻቸውን ያዙ።


ቀርጤስ ተብላ ከምትጠራ ደሴት የመጡ ሕዝቦች በጋዛ አካባቢ የሚኖሩ ኤዋውያን ተብለው የሚጠሩ ነዋሪዎችን ደምስሰው በእነርሱ ቦታ ሰፈሩ።]


ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ የጎሼንን አካባቢ ሁሉ ጨምሮ፥ እስከ ገባዖን ድረስ ወግቶ ድል አደረገ።


እንዲሁም በግብጽ ወሰን እስከሚገኘው ወንዝና እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ ድረስ የሚደርሱ ታናናሽ ከተሞችና መንደሮች ያሉአቸው አሽዶድና ጋዛ ተብለው የሚጠሩ ከተሞች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች