Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 10:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፤ ጨረቃም ካለችበት ሳትንቀሳቀስ ቈየች፤ ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። ሳይንቀሳቀስ በሰማይ መካከል ቆመ፤ ቀኑንም ሙሉ ሳይጠልቅ ቈየ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪበቀል ድረስ፣ ፀሓይ ባለችበት ቆመች፤ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። ፀሓይ በሰማዩ መካከል ቆመች፤ ለመጥለቅም ሙሉ ቀን ፈጀባት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመች፥ ጨረቃም ዘገየች። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ጸንታ ቆመች፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠፋ ድረስ ፀሐ​ይና ጨረቃ በየ​ቦ​ታ​ቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽ​ሐፍ በጊ​ዜው ተጻፈ። ፀሐ​ይም በሰ​ማይ መካ​ከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አል​ጠ​ለ​ቀ​ችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 10:13
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ፍላጻ ከሚወረወረውና እንደ ጦር ከሚያንጸባርቀው መብረቅህ የተነሣ ፀሐይና ጨረቃ በየቦታቸው ቆሙ።


ንጉሥ አካዝ ባሠራው የመወጣጫ ደረጃ ላይ የሚያርፈውን ጥላ እግዚአብሔር እንደገና ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ እንዲመለስ ያደርገዋል።” ጥላውም ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ ተመለሰ።


እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት፥ እንደዚያ ያለ ቀን፥ ከዚያም በፊት ሆነ ከዚያ ወዲህ ታይቶ አይታወቅም፤ በእርግጥም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጐን ተሰልፎ ይዋጋላቸው ነበር።


ከዚህ በኋላ ሶምሶን “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አስበኝ፤ አምላኬ ሆይ! እባክህ ኀይል ስጠኝና ፍልስጥኤማውያን ዐይኖቼን ስላወጡ አንድ ጊዜ ብቻ እንድበቀላቸው አድርገኝ!” ብሎ ጸለየ።


እግዚአብሔር ታዲያ፥ ሌት ተቀን እየጮኹ ለሚለምኑት ሕዝቦቹ አይፈርድላቸውምን? ችላ በማለትስ ርዳታውን ያዘገይባቸዋልን?


በዚያን ቀን ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ያጣሉ።


በፊታቸው ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ ሰማይም ይናወጣል፤ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ብርሃን የማይሰጡ ይሆናሉ።


ፀሐይና ጨረቃ አመስግኑት። የምትበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፤


ነገር ግን መልእክታቸው ወደ ዓለም ሁሉ ይሠራጫል፤ እስከ ምድር ዳርቻም ይደርሳል፤ እግዚአብሔር የፀሐይን መኖሪያ በሰማይ አደረገ።


ትእዛዙም በየሀገሩ እንደ ሕግ ሆኖ እንዲታወጅና ማንኛውም ሕዝብ እንዲገነዘበው ሆነ፤ በዚህ ዐይነት አይሁድ ያ ዕለት በሚደርስበት ጊዜ በጠላቶቻቸው ላይ የበቀል እርምጃ መውሰድ ይችሉ ዘንድ ሁኔታው ተመቻቸላቸው።


የይሁዳም ሕዝብ ያጠኑት ዘንድ አዘዘ፤ ቅኔውም በያሻር መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፦


የሠራዊት እምላክ ስለሚነግሥ ጨረቃ ትጨልማለች፥ ፀሐይም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ እርሱ በኢየሩሳሌም፥ በጽዮን ተራራ ላይ ሆኖ ያስተዳድራል፤ የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።


መሪዎች እስራኤልን ስለ መሩ፥ ሕዝቡም በፈቃደኛነት ራሱን ስላቀረበ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


አሞራውያን በመተላለፊያው ቊልቊለት ከእስራኤላውያን ሠራዊት በሚሸሹበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር እስከ ዐዜቃ ድረስ ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ ስለዚህም እስራኤላውያን ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶው ድንጋይ የሞቱት እጅግ ብዙዎች ነበሩ።


“በእስራኤል ሕዝብ ላይ ስለ ፈጸሙት በደል ምድያማውያንን ቅጣ፤ ይህንንም ካደረግህ በኋላ አንተ ትሞታለህ።”


የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላትና በጉ መብራትዋ ስለ ሆነ ከተማይቱ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጋትም።


አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፥ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ፥ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛቸው ጨለመ፤ በዚህ ዐይነት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛ ያለ ብርሃን ሆነ።


ከዚህ በኋላ በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለከትኩ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይ እንደ ጥቊር የሐዘን ልብስ ጠቈረች፤ ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች፤


እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።


ታላቁና አስገራሚው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች።


ይህን ብታደርጉ፥ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣል፤ እንዲሁም ለጻድቃንና ለግፈኞች ዝናቡን ያዘንባል።


ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር መሪነት ስለ ተደረገው ጦርነት በሚናገር የታሪክ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎአል፦ “በሱፋ ክልልና በሸለቆዎች ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ፥ የአርኖን ወንዝ፥


“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።


ታላቁና አስፈሪው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች፤


ሕዝቅያስም “ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ማድረግ ይቀላል፤ ስለዚህ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አድርግልኝ” አለው።


ፀሐይ እንዳትወጣ ሊያደርግ ይችላል፤ ከዋክብትም እንዳያበሩ ያደርጋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች