ዮናስ 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩትም ሁሉ እርስ በርሳቸው “በዚህ አደጋ ላይ እንድንወድቅ ምክንያት የሆነው ማን እንደ ሆነ ለማወቅ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ከዚያም መርከበኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ለማወቅ፣ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እርስ በእርሳቸውም፦ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደመጣብን እንድናውቅ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እርስ በርሳቸውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ አገኘን እናውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ። ምዕራፉን ተመልከት |