Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚያም ሠላሳ ስምንት ዓመት ሙሉ የታመመ አንድ ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በዚያም ለሠላሳ ስምንት ዓመት ሕመምተኛ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በዚ​ያም ከታ​መመ ሠላሳ ስም​ንት ዓመት የሆ​ነው አንድ ሰው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 5:5
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም የልጁን አባት፥ “ይህ በሽታ ከጀመረው ምን ያኽል ጊዜ ነው?” ሲል ጠየቀው። አባትየውም እንዲህ አለ፤ “ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው።


እነሆ፥ የአብርሃም ዘር የሆነች ይህች ሴት ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ ስትሠቃይ ኖራለች፤ ታዲያ፥ እርስዋ ታስራ ከምትሠቃይበት በሽታ በሰንበት ቀን መፈታት አይገባትምን?”


ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋም ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለሐኪሞች በመክፈል ጨርሳ ማንም ሊያድናት አልቻለም።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሰውየውን በቤተ መቅደስ አገኘውና “እነሆ፥ አሁን ድነሃል፤ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአት አትሥራ” አለው።


አልፎ አልፎ የጌታ መልአክ ወደ ኲሬው ወርዶ ውሃውን ያናውጥ ነበር፤ ከውሃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ ወደ ኲሬው የሚገባ ካደረበት ከማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር።]


ኢየሱስ ይህን ሰው እዚያ ተኝቶ አየውና ከብዙ ጊዜ ጀምሮ መታመሙን ዐውቆ፥ “መዳን ትፈልጋለህን?” አለው።


ኢየሱስ በመንገድ ሲያልፍ ዕውር ሆኖ የተወለደ ሰው አየ።


ነገር ግን አሁን እንዴት እንደሚያይና ዐይኖቹንም ማን እንደአበራለት አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ በዕድሜው ሙሉ ሰው ስለ ሆነ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።”


በልስጥራ እግሩ የሰለለ አንድ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው ከተወለደ ጀምሮ ሽባ ስለ ነበር በእግሩ ሄዶ አያውቅም፤


እዚያ “ውብ” እየተባለ የሚጠራ በር ነበር፤ ሲወለድ ጀምሮ ሽባ የሆነውን አንድ ሰው ሰዎች በየቀኑ እያመጡ እዚያ ያስቀምጡት ነበር፤ እርሱ እዚያ ተቀምጦ ወደ ቤተ መቅደስ ከሚገቡት ሰዎች ምጽዋት ይለምን ነበር።


በዚህ ተአምር የተፈወሰው ያ ሰው ዕድሜው ከአርባ ዓመት በላይ ነበር።


እዚያም ስምንት ዓመቶች ሙሉ በአልጋ ላይ የተኛ ኤኒያ የሚባለውን ሽባ አገኘ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች