Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደምትገኝ፥ ሲካር ተብላ ወደምትጠራ የሰማርያ ከተማ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ በሰማርያ፣ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደ ነበረች፣ ሲካር ወደምትባል ከተማ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትገኝ ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ያዕ​ቆብ ለልጁ ለዮ​ሴፍ በሰ​ጠው በወ​ይን ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ወደ አለ​ችው ሲካር ወደ​ም​ት​ባ​ለው የሰ​ማ​ርያ ከተማ ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 4:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ድንኳኑን የተከለበትን የሴኬም አባት ከነበረው ከሐሞር ዘሮች ላይ በመቶ ብር ገዛው፤


በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኩትን ለሙን ምድር ሴኬምን፥ ከወንድሞችህ ጋር ከምታገኘው ድርሻ በላይ ለአንተ ብቻ ሰጥቼሃለሁ።”


በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይና በሰማርያ ታናናሽ ከተሞች በየኮረብታው ባሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይህ የእግዚአብሔር ነቢይ የተናገረው የትንቢት ቃል በእርግጥ ይፈጸማል።”


ከእርሱ በፊት ቀድመው የሚሄዱትንም መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ሁሉን ነገር ለማዘጋጀት በሰማርያ ወደምትገኘው ወደ አንዲት መንደር ሄዱ።


አንተ ይህን ጒድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እርሱና ልጆቹ፥ ከብቶቹም ከዚህ ጒድጓድ ጠጥተዋል።”


ሴትዮዋ “የሠራሁትን ነገር ሁሉ ነገረኝ” ብላ በመሰከረችው መሠረት ከዚያ ከተማ ብዙዎቹ የሰማርያ ሰዎች አመኑ።


በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስ መንገድ ከመሄድ የተነሣ ስለ ደከመው በጒድጓዱ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ።


በዚያን ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበር።


የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም በሴኬም ተቀበረ፤ ይህም ምድር ያዕቆብ የሼኬም አባት ከሆነው ከሐሞር ልጆች በአንድ መቶ ጥሬ ብር የገዛው ነበር፤ ምድሩም የሚገኘው በዮሴፍ ዘሮች የርስት ድርሻ ክልል ውስጥ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች